አሜሪካ ያቀረበችው የ20 ቢሊዮን ዶላር መድህን

Date:

በኢራን እና በአሜሪካ መካከል እየተካሄደ ያለው ወታደራዊ ፍጥጫ የቀጣናውን የባህር ላይ ንግድ ስጋት ላይ በጣለበት በዚህ ወቅት፣ ዋሽንግተን በሆርሙዝ ሰርጥ ለሚንቀሳቀሱ የነዳጅ እና የጋዝ ጫኝ መርከቦች የ20 ቢሊዮን ዶላር የመድህን ዋስትና ማቅረቧን አስታወቀች።

የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ፋይናንስ ኮርፖሬሽን (DFC) እንደገለጸው፣ ይህ ውሳኔ በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀጥተኛ ትዕዛዝ የተላለፈ ሲሆን፣ ዓላማውም በጦርነቱ ስጋት ምክንያት የተረበሸውን የንግድ መርከቦች በራስ መተማመን መመለስ ነው።

በዓለም አቀፍ ደረጃ 20 በመቶ የሚሆነው የነዳጅ ፍጆታ የሚያልፍበትን የሆርሙዝ ሰርጥ የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ለአሜሪካና ለአጋሮቿ መዝጋቱን ተከትሎ፣ ይህ አዲስ የመድህን ዕቅድ በመርከቦች አካል፣ በማሽነሪዎች እና በጭነት ላይ ለሚደርሱ አደጋዎች የፋይናንስ ጥበቃ በመስጠት የዓለም የኃይል አቅርቦት መቋረጥን ለመከላከል ያለመ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ተደርጎ ተወስዷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...