አዋሽ ባንክ ባለፈው ሐምሌ ወር ለደንበኞቹ ከ125 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ እንዳቀረበ አስታዉቋል።
ይህንን ያደረገው በሀገሪቱ ያለውን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለመቅረፍ እና የደንበኞችን ፍላጎት ለማሟላት በሚደረገው ጥረት አካል ነው ብሏል።
ከቀረበው አጠቃላይ ገንዘብ ውስጥ ከ70 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለነዳጅ ግዢ ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን፣ ቀሪው 55 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ለሌሎች ስልታዊ እቃዎች (strategic commodities) ድልድል ተደርጓል።
ባንኩ ለትምህርት እና ለህክምና አገልግሎቶችም ቅድሚያ በመስጠት የውጭ ምንዛሬ መመደቡን ገልጿል።
ባንኩ በቀጣይም በእጁ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሪ በስፋት እያቀረበ የሚቀጥል መሆኑንም አስታውቋል ።
