አዲሱ የምርጫ ቦርድ ደንብ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ቅሬታ ቀሰቀሰ

Date:

ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የወጣው አዲሱ የምርጫ ሥነ-ምግባር ደንብ፣ ለፖለቲካ ቅስቀሳ ምቹ ያልሆኑና የፓርቲዎችን ነጻነት የሚገድቡ ድንጋጌዎች እንዳሉበት ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ (ኢብዴአፓ) እና የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) እንደገለጹት፣ በተለይ በመገናኛ ብዙኃን አጠቃቀም ረገድ የተቀመጡት ገደቦች የፓርቲዎችን የሐሳብ ነጻነት የሚገድቡና በመንግሥት ሚዲያዎች በሚደረጉ ክርክሮች ላይ ቃላት እስከመምረጥ የሚደርስ ጫና የሚፈጥሩ ናቸው።

በሌላ በኩል፣ ደንቡ ፓርቲዎች ማኅበረሰቡን በጥቅማ ጥቅም እንዳይደልሉ መከልከሉ እንደ በጎ ጎን የተነሳ ቢሆንም፣ የቁጫ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁሕዴፓ) ግን ገዢው ፓርቲ ደንቡን በመጣስ የሌሎችን አቅም እያዳከመ መሆኑን ወቅሷል።

ቦርዱ ደንቡን ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ለማካሄድ ወሳኝ መሆኑን ቢገልጽም፣ ፓርቲዎቹ ግን በደንቡ ጥሰት ምክንያት የሚከተለው ቅጣትና በቅስቀሳ ወቅት የሚገጥሟቸው ተግዳሮቶች የምርጫ ሂደቱን ሊያቀዘቅዙት እንደሚችሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...