አዲስ ቱሞሮ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ከአምስት ሀገር በቀልና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ስምምነት ፈፀመ

Date:

አዲስ ቱሞሮ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በምዕራፍ አንድ የግንባታ ሂደት የተካተቱ አገልግሎቶችን የሥራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር አካሂዷል።

ኢኮኖሚ ልዩ ዞኑ መዋዕለ ንዋያቸውን በአዲስ ቱሞሮ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ለማፍሰስ ፍቃደኛ ከሆኑ አምስት ሀገር በቀል እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ስምምነት ፈፅሟል።

በመንግሥት እና የግል አጋርነት የሚመራው የኢኮኖሚ ልዩ ዞኑ የአፓርትመንት ቤቶች ሽያጭ ያስጀመረ ሲሆን፤ በምዕራፍ አንድ የግንባታ ሂደቱ አፓርትመንት እንዲሁም የንግድ ተቋማትን አጣምሮ በ45 ሺህ ሜትር ስኩዌር ስፍራ ላይ ይገነባል።

አዲስ ቱሞሮ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ለመዲናዋ አዲስ ገፅታ የሚያላብስ፣ ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነቷን የሚያጎላ እና ተጨማሪ የውበት ምንጭ ይሆናል ነው የተባለው፡፡

በአዲስ አበባ ጎተራ አካባቢ እየተገነባ የሚገኘው አዲስ ቱሞሮ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን የምዕራፍ አንድ ሥራውን በቀጣይ ዓመት ታህሳስ ወር ላይ እንደሚጠናቀቅ ተጠቁሟል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአዲስ ቱሞሮ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታን ነሐሴ 6 ቀን 2016 ዓ.ም የመሠረት ድንጋይ በማስቀመጥ ማስጀመራቸው ይታወሳል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...