አዲስ የሰው ልጅ  ቅሪተ አካል ተገኘ

Date:

በአፋር ክልል ሌዲ ገራሩ አካባቢ ከ2.6 እስከ 2.8 ሚልዮን ዓመት ያስቆጠረ የአውስትራሎፒቴከስ የተባለ የሰው ልጅ አዲስ ቅሪተ አካል ተገኘ።

የአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ የጥናት ቡድን በአካባቢው ባደረገው ምርምር 13 ጥርሶችን ያገኘ ሲሆን ዝርያውም አዲስ መሆኑን ተነግሯል።

በአካባቢው ከዚህ ቀደም የሰው ልጅ ቅሪተ አካል ተገኝቷል ተብሏል።

ግኝቱም በሳይንስ ጆርናል በሆነው ኔቸር ጆርናል ላይ ታትሞ የወጣ መሆኑን ተጠቅሷል።

አዲሱ አውስትራሎፒቴከስ ይፋዊ ስም እንዳልተሰጠው የጥናት በድን ተሳታፊ የሆኑት ፕሮፌሰር ኤም ሬክቶር ተናግረዋል።

አዲስ ስም ለመስጠት ተጨማሪ ቅሪተ አካል መገኘት አለበት ምርምሩም ይቀጥላል ብለዋል።

አዲስ የተገኘው አውስትራሎፒቴከስ ዝርያ ከዚህ ቀደም ከተገኘው አውስትራሎፔቲከስ አፋሬንሲስ እንደሚለይ ተነግሯል።

ቅሪት አካሉ በተገኘበት አካባቢ የሰው ልጅ ከሚልዮን ዓመታት በፊት እንደሚኖርበት ጥሩ ማመሳከሪያ ነው ተብሏል።
ሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...