የእስራኤል መንግሥት እንግሊዝ በሚቀጥለው ወር ለፍልስጤም እውቅና እሰጣለሁ ማለቷን ተከትሎ እርምጃውን እንደ አንድ አማራጭ እያጤነው እንደሆነ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።
“ለንደን ጥንቃቄ ማድረግ አለባት ምክንያቱም ቢቢ [የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ] እና ሚኒስትሮቻቸው መጫወት የሚችሉባቸው ካርዶች አሏቸው። እስራኤል ከዩናይትድ ኪንግደም ጋር ያላትን አጋርነት ከፍ አድርጋ ትመለከታለች፤ ነገር ግን የቅርብ ጊዜ ውሳኔዎች አጋርነቱ ጫና ውስጥ እንደገባ እና የእስራኤል መንግሥት እርምጃዎችን ለመውሰድ ከወሰነ ዩናይትድ ኪንግደም ብዙ የምታጣቸው ነገሮች አሉ” ሲል የብሪታንያ ጋዜጣ ዘግቧል።
የእስራኤል የፀጥታ ካቢኔ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ሃማስን ለመደምሰስ በሚል ሠራዊቱ ጋዛ ከተማን እንዲቆጣጠር ያቀረቡትን እቅድ አርብ አጽድቋል።
ካቢኔው በአብላጫ ድምጽ አምስት መርሆችን አጽድቋል፡፡ ሀማስን ትጥቅ ማስፈታት፣ 50 ታጋቾችን መመለስ፣ የጋዛን ሰርጥ ከጦር ኃይል ነፃ ማድረግ፣ የእስራኤል የጸጥታ ቁጥጥር እና ከሀማስ እና ከፍልስጤም አስተዳደር ወጪ መንግሥት መመስረት።
