እስራኤልና ኢራን የአየር ክልላቸውን ሙሉ ለሙሉ ዘጉ

Date:

እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት መፈጸሟን ተከትሎ የአየር ክልሏን ለማንኛውም በረራ ዝግ ማድረጓን አስታውቃለች።

አሜሪካ በኢራን ላይ ጥቃት ልትሰነዝር እንደምትችል ስጋት የገባቸው በርካታ አገራት አርብ ዕለት በአካባቢው ላሉ ዜጎቻቸው ማስጠንቀቂያ ሰጥተው ነበር።

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዛሬ ማለዳ በኢራን ላይ ጥቃት መሰንዘሩን አስታውቋል።

ዩናይትድ ኪንግደም በቴህራን ከሚገኘው ኤምባሲዋ ሠራተኞቿን ያስወጣች ሲሆን፣ ወደ እስራኤልም “አስፈላጊ ከሆኑት በስተቀር ሁሉም ጉዞዎች” እንዳይደረጉ በሚል መመሪያዋን አሻሽላለች።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ በኢራን የሚገኙ ዜጎቿን “በፍጥነት” ለቅቀው እንዲወጡ አሳስባ ነበር።

ቻይና፣ ሕንድ እና ካናዳን ጨምሮ ሌሎች አገራት ዜጎቻቸው ጦርነቱ ሊከሰት ስለሚችል በተቻለ ፍጥነት ከኢራን ለቅቀው እንዲወጡ ያሳሰቡት ከጥቃቱ ቀደም ብለው ነው።

ጀርመን ዜጎቿ ወደ እስራኤል እንዳይጓዙ ስትመክር ፈረንሳይ ደግሞ ባይጓዙ መልካም መሆኑን ለዜጎቿ ገልጻለች።

ኢራን የአየር ክልሏን ለየትኛውም በረራ ዝግ አደረገች

ኢራን በመላው አገሪቱ ምንም ዓይነት የአውሮፕላን በረራዎች እንዳይካዱ የአየር ክልሏን ዝግ አደረገች።

የኢራን ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን ቃል አቀባይ ማጂድ አክሃቫን የኢራን የአየር ክልል “ተጨማሪ መግለጫ እስኪሰጥ ድረስ” ዝግ መደረጉን አስታውቀዋል።

የኢራን ባለሥልጣናት ይህንን ከማሳወቃቸው በፊት እስራኤል ለየትኛውም የንግድ አውሮፕላን በረራ የአየር ክልሏን መዝጋቷን ይፋ አድርጋ ነበር።

ከኢራን መንግሥት ጋር ግንኙነት ያለው ታስኒም የዜና ወኪል አገሪቱ የአየር ክልሏን መዝጋቷን ዘግቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...