ከተማ አቀፍ የማንበብና መጻፍ (ሊትሬሲ) ቀን እየተከበረ ይገኛል

Date:


በአዲስ አበባ ከተማ የማንበብና መጻፍ ቀን በአብርሆት ቤተ መፃህፍት እየተከበረ ይገኛል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት አምባሳደር ፍፁም አረጋ በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ የዲያስፖራው ማህበረሰብ አባላት መፃሕፍትን አሰባስበው እና የሎጂስቲክስ ወጭውን ችለው ለቤተመጽሀፍቱ መላካቸውን ገልጸዋል።

አምባሳደሩ የዲያስፖራው ማህበረሰብ አባላት በሀገር ውስጥ ዕውቀት እንዲሰፋ የመፅሐፍት ድጋፍ ማድረጋቸው ትልቅ አስተዋፅዖ እንደሚኖረው ገልጸው መጽሀፍ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

የአብርሆት ቤተ መፃሕፍት ዳይሬክተር ሙሉቀን ታሪኩ ቤተመፃህፍቱ በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ አሁን ካለበት ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል።

ዳይሬክተሩ ከአሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ሳውዲ አረቢያና ኬንያ ከዲያስፖራው ማህበረሰብ የተለያየ ዘርፍ ላይ ያተኮሩ መፅሐፍት ለቤተ መፅሃፍቱ መቅረባቸውን አስታውቀዋል።

ቤተመፃህፍቱ ለተለያዩ የሀገር ውስጥ ቤተ መፃህፍት ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም አስታውቀዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የዲያስፖራው ማህበረሰብ አባላት በሀገራችን ዕውቀት እንዲሰፋ የሚያደርጉትን የመፅሐፍ ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጠይቋል።

NBCEthiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...