ከአቦካዶ ዘይት ኤክስፖርት 3 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኘ

Date:


በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ወደ ውጭ ከተላከ የአቦካዶ ዘይት ከ3 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።

የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ኃይሉ ዬተራ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ የኢንዱስትሪ ፓርኩ በአጠቃላይ 32 ፕሮጀክቶች ይገኛሉ። ስምንቱ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ወደ ፓርኩ የተቀላቀሉ አዳዲስ ፕሮጀክቶች ናቸው፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 16 ሺህ ቶን የጥሬ ዕቃ ግብዓት ወደ ፓርኩ ገብቶ እንደተቀናበረ ገልጸው፤ በዚህም ወደ ውጭ ከተላከው የአቦካዶ ዘይት ብቻ 3 ነጥብ 36 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን አመልክተዋል።

300 ሺህ ዶላር የሚያወጣ ተኪ ምርትም ለሀገር ውስጥ ገበያ መዋሉን አቶ ኃይሉ ገልፀዋል።   አጠቃላይ 137 ሺህ ለሚሆኑ አርሶ አደሮች በይርጋለም አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የገበያ ትስስር መፈጠሩን አስረድተዋል፡፡

ጋዜጣ_ፕላስ |

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...