የ5 ግዜ የባሎን ዶር አሸናፊው ክርስትያኖ ሮናልዶን በታዋቂው የአሜሪካ ተከታታይ ፊልም ‘ Fast & Furious ‘ ላይ ልንመለከተው እንደምንችል አሜሪካዊው የፊልም ተዋናይ ቪን ዲዝል አስታውቋል ።
በፊልሙ ላይ መሪ ተዋናዩን ዶሚኒክ ቶሬቶን ሆኖ የሚጫወተው ቪን ዲዝል የአል ናስሩን አጥቂ ‘ Fast Forever ‘ ይሰኛል በተባለው የፊልሙ የመጨረሻ እና 11 ኛው ክፍል ላይ ልንመለከተው እንደምንችል ገልጿል ። ዲዝል በኢንስታግራም ገፁ በፊልሙ ላይ ለሮናልዶ የሚሆን ገፀ ባህሪ መፃፉን አስታውቋል ።
የፊልሙ አዘጋጆች ግን እስካሁን ክርስትያኖ ሮናልዶ በፊልሙ ስለመሳተፉ ማረጋገጫ አልሰጡም ።
በእግር ኳስ ህይወቱ ማብቂያ ላይ የሚገኘው የ40 አመቱ ክርስትያኖ ሮናልዶ ከኳስ በኋላ ለሚኖረው ህይወቱ እየተዘጋጀ ነው የተባለ ሲሆን ባለፈው ሚያዝያ ከእንግሊዛዊው ታዋቂ ፕሮዲዩሰር ማቲው ቮህን ጋር በመሆን የራሱን የፊልም ስቱድዮ መክፈቱ ይታወሳል ።
