የሐጅ ሥርዓት ከጅማሮ እስከ ፍፃሜ

Date:


ሙስሊሞች በፈጣሪያቸው ዘንድ ምንዳ የሚያገኙበት፣ አብሮነትን የሚያጠናክሩበት፣ ከሌሎች ሀገራት ወንድም እህቶቻቸውን የሚተዋወቁበት፣ ፈጣሪያቸውን የሚያወድሱበት፣ ከእስልም እና መሠረቶች አንዱ ነው – የሐጅ ጸሎት ሥርዓት።

እስካሁን ከመላው ዓለም በሁሉም የትራንስፖት ዓይነት ማለትም ከ1.2 ሚሊዮን በየብስ፤ ከ63 ሺህ በላይ በአየር፤ ከ5 ሺህ በላይ ደግሞ በባሕር በድምሩ ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ሙስሊሞች የሕይወት ዘመናቸው ሕልም የሆነውን ሐጅ ለመፈፀም ሳዑዲ ዓረቢያ መካ ከተማ ድረሳቸውን የሀገሪቱ የሐጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር ገልጿል።

የ1446ኛው ዓመተ ሒጅራ የሐጅ ሥርዓት በዛሬው ዕለት ሲጀመር ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ሙስሊሞች ለሚቀጥሉት ቀናት ሐጅ ሚያደርጉ ይሆናል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጽ/ቤት ኃላፊ ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ በተለይም ለኢቢሲ ዶትስትሪም እንደገለጹት፣ አቅም እና ፍላጎት ያለው ማንኛውም ሙስሊም ሰው ሐጅ ለመፈፀም ከሚሠራቸው ተግባራት መካከል (ኢህራም) ነጭ ልብስ ለብሶ ከቤት መውጣት አንዱ ነው።

ይህም ሰዎች ምድራዊ ሀብታቸውን እና ሥልጣናቸውን ሁሉ ትተው ሲሞቱ የሚለብሷትን ነጭ ልብስ ብቻ በመልበስ ደሃውም፣ ሀብታሙም፣ መሪውም ተመሪውም፤ ነጠላ ጫማ እና ሽርጥ አድርገው፣ አንድ ዓይነት አለባበስ ለብሰው ‘ለበይክ’ (የፈጣሪን ጥሪ መልስ ሰምቻለሁ) እያሉ የአላህን አንድነት እየመሰከሩ የሚፈፀም ነው ይለሉ ኡስታዝ አቡበከር።

‘ኢህራም’ (ነጭ ልብስ) በልብ ውስጥ ሐጅ ለማድረግ ማሰብ (ኒያ) ለ’ሑጃጆች’ አስፈላጊ ሲሆን በአራቱም አቅጣጫዎች በሮች መኖራቸውን፣ ኢትዮጵያውያን የሚገቡበት በርም የለምለም በር ተብሎ እንደሚጠራ ነግረውናል።

‘ሑጃጆች’ መካ ሲድርሱ የመጀመሪያ የሐጅ ሥራቸው ካዕባን (የአላህ ቤት) ሰባት ጊዜ በመዞር (ጠዋፍ) በማድረግ እንደሆነ ገልጸዋል።

ቀጥሎም ‘ሶፋ’ እና ‘መርዋ’ ላይ ፈጣሪያቸውን እየለመኑ 7 ጊዜ የሚመላለሱ ሲሆን፣ በዚህ የሐጅ የመጀመሪያ ምዕራፍ መጨረሻ ላይ ‘ሑጃጆች’ ወንዶች ፀጉራቸውን አሳጥረው፣ ልብሳቸውን በመቀየር ወደ መደበኛ ሕይወት ይገባሉ ብለዋል።

በዙልሂጃ ወር 8ኛ ቀን ሁሉም ‘ሑጃጆች’ ካረፉቡት ተነሥተው ‘መቢት ሚና’ ለማድረግ ወደ የዓለማችን ትልቋ የድንኳን ከተማ ‘ሚና’ ሄደው ጸሎት ያደርጋሉ፣ ፈጣሪያቸውን እየለመኑ ያድራሉ ነው ያሉት።

በ9ኛው ቀን ከሚና ከተማ በመነሣት ወደ ዓረፋ ተራራ አቅንተው የዙህር እና የአሥር ሶላታቸውን ይሠግዳሉ። ‘ኩጥባ’ም ይደረጋል። ፈጣሪያቸውን እየለመኑ እና እያመሰገኑ ጊዜያቸውን በኢባዳ ያሳልፋሉ።

ለሁሉም ‘ሑጃጆች’ በዓረፋ ተራራ ክልል ተገኝተው መቆም ሃይማኖታዊ ግዴታ ሲሆን፣ ይህን ያላደረገ ሐጅ የተሟላ አይሆንም ብለዋል። ፀሐይ እስከምትጠልቅ ድረስ ፈጣሪቸውን እንደሚለምኑ ነው የገለጹት።

ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ሁሉም ሑጃጅ ወደ ‘ሙዝደሊፋ’ ተራራ በመምጣት መግሪብ እና እሻ ሶላት ይሠግዳሉ፤ ሌሊቱን እዛው ያሳልፋሉ። በ‘ሙዝደሊፋ’ ተራራ የንጋት ሶላት ሠግደው በ10ኛው የዙልሂጃ ቀን (የዓረፋ ዕለት) ወደ ሚና ይመለሳሉ ብለዋል ኡስታዝ አቡበከር።

ከዚያም ‘ጀምረቱል አቀባ’ ወይም ሰባት ጠጠሮችን በመውሰድ ሸይጣንን በድንጋይ የመምታት (የድንጋይ መወርወር) ተግባር ከውነው ከሚና ወደ መካ በመመለስ፤ ፀጉራቸውን አሳጥረው፣ ገላቸውን ታጥበው፣ ልብሳቸውን ቀይረው ‘ጠዋፍ’ ወይም ጠዋፈል ኢፋዳህ ይፈፅማሉ ብለዋል።

የመጀመሪያው የሐጅ ሥርዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጣዩ 3 ቀናት የዒድ ቀናት ሲሆኑ በሚና ከተማ በመብላት በመጠጣት እየተደሰቱ ያሳልፋሉ።

በዙልሂጃ ወር 10ኛው ቀን እርድ ይፈፅማሉ፤ በሕጉ መሠረትም እኩል ለ3 አካፍለው አንዱን ለምስኪን፣ አንዱን ለጎረቤት ሰጥተው ቀሪውን ለራሳቸው እየበሉ እየጠጡ እየተደሰቱ ያሳልፋሉ።

ሁሉም ‘ሑጃጆች’ 3 ቀናት ፈጣሪያቸውን በማወደስ በመለመን በሚና ከተማ ያሳልፋሉ።

በመጨረሻም ወደ መካ ተመልሰው የስንብት ‘ጠዋፍ’ በማድረግ ወደ የሀገራቸው ይመለሳሉ።

በላሉ ኢታላ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...