“የሕዝበ ሙስሊሙ ምርጫ ሰላማዊ በሆነ መልኩ ተጠናቋል”

Date:

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ዛሬ በአራት ዘርፎች ያደረገው ምርጫ ሰላማዊ በሆኑ መልኩ መጠናቀቁን ም/ቤቱ የላከውን መግለጫ ጠቅሶ ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

የከፍተኛ ም/ቤቱ የ2017 ምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ “ዛሬ  ነሐሴ 11/2017 ዓ/ም በ334 የምርጫ ጣቢያዎች በአራት ዘርፎች ማለትም በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ የወጣቶችና የምሁራን፤ በከሰዓቱ ክፍለ ጊዜ ደግሞ የሴቶችና የሠራተኛው ማህበረሰብ ዘርፎች ሲካሄድ የነበረው የሕዝበ ሙስሊሙ ምርጫ ፍፁም ሠላማዊ በሆነ መልኩ ተጠናቋል” ብሏል።

በተጨማሪም ነሐሴ 9 ቀን 2017 በነበረው የዑለሞች ምርጫና በዛሬው ቀን ነሐሴ 11 የተካሄደው የአራት ዘርፎች ምርጫ፤ ፍፁም ሠላማዊ በሆነ መልኩ እንዲከናወን የአዲስ አበባ ሠላምና ፀጥታ ቢሮና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ላደረጉት ድጋፍ በመላው ሕዝበ ሙስሊም ስም ላቅ ያለ ምስጋና ለማቅረብ እንወዳለን ብሏል፤ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...