ፕሬዚዳንቱ በሻንካ’ይ ትብብር ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ነው ወደ ወዳጃቸው ቻይና ብቅ ያሉት።
በአራት ቀናቱ የቻይና ቆይታቸውም ፕሬዚዳን ሺ ጂንፒንግን ፣የህንዱን ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲን ጨምሮ የተለያዩ ነሪዎችን ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሽን’ካይ ትብብር (SCO) ጉባዔ በሚካሄድባት ቲያንጂን ደርሰዋል።
የትብብሩ ጉባዔ በዋናነት በቀጠናዊ ጸጥታ ላይ የሚያተኩር በመሆኑ ትልቅ ዋጋ የሚሰጠውም ሆኗል።
ጃፓን በሁለተኛው ዓለም ጦርነት እጅ የሰጠችበትን 80ኛ የድል በዓል ላይም ፑቲን የሚገኙ ሲሆን ለምዕራቡ ዓለም መልዕክት የሰደደ ውሳኒያቸውም ሆኖላቸል።
በቻይናና ሩሲያ መካከል ያለው ዲፕሎማሲዊ ግንኙነት ወደ ገደብ የለሽ ትስሰር መለወጡም የዓለምን ፖለቲካ ሺ እና ፑቲን ወደ መጠቅለሉ ናቸው እንዲሉም ምራባውያኑን አስገድዷል።
አሜሪካ የአገራቱን የበረታ ወዳጅነት በተለይም የፑቲንንና የሺን ግንኙነት እንዲሁም ኢራንን እና ሰሜን ኮሪያን መሪዎች “የአምባገነኖች ጥምረት ” ትለዋለች።
ለዚህም ነው ፑቲን ወደ ቻይና ማቅናታቸው ከጉዞ ባሻገር ነው እየተባለ ያለው።
በድል በዓሉ ላይ የሰሜን ኮሪያው ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን ይገኛሉ መባሉም ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አገኛቸዋለሁ ያሉበትን ዓላማቸውን ጫና ውስጥ አስገብቶታል።
ቤይጂንግ “የሽሚያ ፖለቲካ” ውስጥ እንደገባች ያሳያል በሚልም ዘ ዋሽንግተን ፖስት በሰፊው ዘግቦታል።
ዘገባው የአር ቲ ነው።
