የቀድሞ ፕሬዚዳንት የሰላም ሂደት እንዲያስተባብሩ ተመረጡ

Date:

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሣሕለወርቅ ዘውዴ፣ የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክን የሰላም ሂደት እንዲያስተባብሩ  ተመረጡ፡፡

የዚምባብዌ መሪ የምሥራቅ ኮንጎ ግጭት ዋና መንስኤ መፍትሄ እንዲያገኝ  ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የደቡብ አፍሪካ የልማት ማኅበረሰብ ሊቀመንበር ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ፤ ከምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ ሊቀመንበር የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር በመሩት የቨርቹዋል ጉባኤ ላይ ነው ጥሪውን ያቀረቡት፡፡

“ክቡራን፤ እህት ሀገር ኮንጎ ዴሞክራሲያው ሪፐብሊክ ያጋጠሟትን ፈተናዎች ለመፍታት በጋራ ባለን ቁርጠኝነት ላይ ለመሳተፍ ጊዜ ስለሰጣችሁን አመሰግናለሁ” ሲሉ ምናንጋግዋ ለአፍሪካ መሪዎች ተናግረዋል፡፡

ጉባኤው አምስት የቀድሞ የአፍሪካ ፕሬዚዳንቶችን በአስተባባሪነት በይፋ ሾሟል፡፡

ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ (ናይጄሪያ)

ኡሁሩ ኬንያታ (ኬንያ)

ካትሪኔ ሳምባ-ፓንዛ (ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ)

ሣሕለወርቅ ዘውዴ (ኢትዮጵያ)

ሞክግዌትሲ ማሲሲ (ቦትስዋና)

ምናንጋግዋ እና ሩቶ፤ የደቡብ አፍሪካ የልማት ማኅበረሰብ (የሉዋንዳ) እና የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ (የኬንያ) የተናጠል የሰላም ሂደቶች ወደ አንድ አፍሪካ መር ተነሳሽነት እንዲዋሃዱ ወስነዋል፡፡

Sputnik-

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...