የተካረረው የህወሓት እና የፌዴራል መንግስቱ መካሰስ የት ይደርስ ይሆን?

Date:

በኢትዮጵያ የፌደራል መንግስት እና በህዝባዊ ወያኔ አርነት ትግራይ (ሕወሃት) መካከል የተፈጠረው እሰጥ አገባ እየተባባሰ የሄደ መስሏል።  ለሁለት ዓመታት የዘለቀውን አስከፊውን ደም አፋሳሽ  ጦርነት በፕሪቶሪያ በተደረሰ የሰላም ስምምነት መግታት የቻሉት ሁለቱ ኃይላት ስምምነቱን አጽንተው ዘላቂ ማድረግ ግን ተስኗቸዋል። በስምምነቱ ማዕቀፉ ውስጥ የተያዙ አንኳር ጉዳዮችን ተግባራዊ ማድረግ ባለመቻላቸውም በመካከላቸው የተፈጠረው መካሰስ እና መወነጃጀል ተባብሷል፤ ሌላ ውጥረት እንዳይፈጠርም  አስግቷል።


የግንቦት 20 አከባበር፣ የዴሞክራስያዊ ስምረት ትግራይ ምሥረታ እና የኢሳያስ አፈወርቂ ንግግር
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ከፖለቲካ ፓርቲነት መሰረዙን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ሕወሓት በበኩሉ የቦርዱን ውሳኔ አይቀበልም። ይልቁኑ “ነባሩ ሕጋዊ የዕውቅና ሰርተፍኬት” እንዲመለስለት ነው የጠየቀው። ከህግ ይልቅ ፖለቲካዊ ውሳኔ የሚፈልገው የፓርቲ ምዝገባ ጉዳይ ውጥረ,ቱን ከሚያባብሱት ጉዳዮች ውስጥ በዋናነት ተጠቃሽ ሳይሆን አይቀርም።


ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ከፖለቲካ ፓርቲነት መሰረዙን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ሕወሓት በበኩሉ የቦርዱን ውሳኔ አይቀበልም።

የቀድሞዉ የትግራይ ጊዚያዊ ፕሬዝደንት የሚመሩት የህወሓት አንጃ አዲስ ፓርቲ መሰረተ
በሌላ በሕወሃት ውስጥ የተፈጠረው የአመራር መከፋፈል በክልሉ ሌላ አዲስ ፓርቲ እንዲወለድ ምክንያት ሆኗል። በክልሉ የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በህወሓት መካከል የተፈጠረው መከፋፈል ከፌደ,ራል መንግስቱ እና ከኤርትራ መንግስት ጋር የሚያብሩ ቡድኖችን ፈጥሮ ክልሉን ለሌላ የጦርነት አውድማ ሊጋብዝ የሚችል ስጋት ደቅኗል ሲሉ ይከሳሉ ።


በክልሉ የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በህወሓት መካከል የተፈጠረው መከፋፈል ከፌደ,ራል መንግስቱ እና ከኤርትራ መንግስት ጋር የሚያብሩ ቡድኖችን ፈጥሮ ክልሉን ለሌላ የጦርነት አውድማ ሊጋብዝ የሚችል ስጋት ደቅኗል ሲሉ ይከሳሉ

አንድ ለአንድ- የሕወሓት ከፖለቲካ ፓርቲነት መሰረዝ እና ቀጣይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ
የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተከትሎ የሻከረው የኢትዮ ኤርትራ ግንኙነት በኢትዮጵያ የባህር በር መሻት ጉዳይ አዲስ ቀጣናዊ ውጥረት አስከትሏል። የፌደራል መንግስቱ በሚያስተዳድራቸውም ሆነ ለመንግስት ቅርበት ባላቸው የመገናኛ ብዙኃን የህወሓት ባለስልጣናት ከኤርትራ መንግስት ጋር ግንኙነት እየፈጠሩ ነው ሲሉ ይከሳሉ ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከህዝባዊ በዓልነት ያገደውን የግንቦት 20 የድል ቀንን በተናጥል ያከበረው የትግራይ ክልል ብቻ መሆኑ እና ኤርትራን የሚመለከቱ ጉዳዮች በበዓሉ ላይ መስተጋባታቸው ህወሃት ከፌደራል መንግስቱ ጋር ያለውን የግንኙነት ሁኔታ ሳያባብስ እንደማይቀር ይገመታል።

Dw Amharic

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...