የታሪክ አፍታ

Date:

ልክ በዛሬዋ ቀን ሰኔ 5 1956ዓ.ም የፀረ አፓርታይድ ታጋዩ እና የደቡብ አፍሪካው የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ፓርቲ መሪው ኔልሰን ማዴላ የዕድሜ ልክ እስራት የተበየነባቸው ቀን ነበር፡፡

በአገር ክህደት ወንጀል እና በህገወጥ መንገድ ከአገር ለመውጣት በመሞከር በተደጋጋሚ በሮበን ደሴት እስር ቤት ሲታሰሩ ሲፈቱ የነበረ ሲሆን በኋላም አሻጥር ፈፅመዋል በሚል  ኔልሰን ማንዴላ የዕድሜ ልክ እስራት ተበየነባቸው።

ማንዴላ ጠባብ በሆነች ክፍል ያለማረፊያ ከከባድ የጉልበት ስራ ቅጣት ጋር ሲሰቃዩ ኖረው መጨረሻ ላይ አገራቸውን ከአፓርታይድ አገዛዝ ነፃ አውጥተው ፕሬዝዳንት እስከመሆንም ደርሰዋል፡፡

በዚህ ድርጊታቸውም የሰላም ኖቤል ተሸላሚ የሆኑ አፍሪካዊ መሪ ሆነው ነበር።

ማንዴላ በጥቂት ነጮች የበላይነት የተያዘውን የመንግስት እና የዘር መድሎን በመቃወም ከህጋዊ ሰላማዊ የፓርቲ ትግል እስከ የደፈጣ ትግል በማድረግ ያሰቡትን ዓላማ አሳክተዋል፡፡

የፀረ አፓርታይድ ታጋዩ እና የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ፓርቲ መሪው ኔልሰን ማዴላ በ95 አመታቸው እ.ኤ.አ በታህሳስ 5 2013 በደቡብ አፍሪካ አርፈዋል።

Nbc_Ethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...