የአውሮፓ ህብረት ለአፍሪካ የ58.4 ቢሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ሊያደርግ ነው

Date:

የአውሮፓ ህብረት ለ2028-2034 ባለው ጊዜ ውስጥ ለውጭ ሀገራት ተግባራት ከተመደበው ጠቅላላ በጀት ውስጥ ትልቁን ድርሻ ለአፍሪካ ለመስጠት ማቀዱን አስታውቋል።

የቀረበው ረቂቅ በጀት እንደሚያሳየው፣ አፍሪካ 58.4 ቢሊዮን ዩሮ (68.35 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር) የገንዘብ ድጋፍ ልታገኝ ነው።

ይህ የገንዘብ ድጋፍ የህብረቱን የውጭ ጉዳይ የገንዘብ ድጋፍ ወደ አንድ ነጠላ መሣሪያ ለማዋሃድ በታቀደው “ግሎባል አውሮፓ” (Global Europe) በሚባለው አዲስ ፕሮግራም በኩል የሚሰጥ ነው።

የአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ድጋፉን በዋናነት ለመሠረተ ልማት ዝርጋታ እና የአካባቢ ኢኮኖሚን ለማሳደግ እንደሚጠቀምበት ገልጿል። ይህም ከኢኮኖሚ ውድቀት እና ሥራ አጥነት የሚመነጨውን ሕገወጥ ስደት ለመቀነስ ያለመ መሆኑን ቅዳሜ ገበያ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል ።

KGEthiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...