በአገራችን የተመረጡ ክልሎች እና አዲስ አበባ ላይ ጥናቱ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
በአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአዕምሮ ህክምና ትምህርት ክፍል ስር የሚገኘው እስኮፕ ፕሮጀክት ጥናቱን የሚያከናውን ይሆናል።
በጥናቱ የአዕምሮ ህመሙ ያለበትን ነባራዊ ሁኔታዎችን በማጥናት የተሻለ የህክምና አገልግሎት ተደራሽነት፣ የታማሚዎችን እና ቤተሰቦቻቸውን ጤና እና ኑሮ በማሻሻል ምርምር እንደሚደረግ ተገልጿል።
በጥናቱ የሚሳተፉት የአዕምሮ ህሙማን እና ቤተሰቦቻቸው ከማህበረሰቡ ውስጥ የሚመረጡ እንደሆነም ተነስቷል።
ጥናቱ ፅኑ የአዕምሮ ህመም ያለባቸውን ሰዎች በመለየት በቶሎ እርዳታ እንዲያገኙ እና የተሻለ ህይወት መምራት እንዲችሉ የሚያደርግ ነው ተብሏል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና በኦሮሚያ በተመረጡ ወረዳዎች እና በአዲስአበባ ቂርቆስ እና ልደታ ክፍለከተሞች ላይ ጥናቱ ይካሄዳል።
እነዚህ ቦታዎች የተመረጡበት ምንም የተለየ ምክንያት እንደሌለም ተገልጿል።
ለ25 አመታት በአሁኑ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተለይ ቡታጅራ ላይ ስለ አዕምሮ ጤና ሲሰራ ቆይቷል ሲሉ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶክተር ውብዓለም ክልሉ የተመረጠበትን ምክንያት አብራርተዋል።
ኦሮሚያ ክልል ላይም ባለው የፀጥታ ሁኔታ ተደራሽ መሆን የሚቻልባቸው ቦታዎች ላይ ጥናቱ እንደሚደረግ አንስተዋል።
ቂርቆስ እና ልደታ ክፍለከተሞችም የተመረጡት የበለጠ ተጋላጭነት ስላለባቸው ሳይሆን ፤ እነዚህ ቦታዎች ላይ በመስራት ቀሪውን ለመንግስት ለመስጠት በመታሰቡ ነው ብለዋል።
ጥናቱ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል።
