የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ፤ከአዕምሮዓዊ ንብረት ባለስልጣን የፈጠራ ባለቤትነት መብት አገኘ

Date:

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ፤
ከአዕምሮዓዊ ንብረት ባለስልጣን የፈጠራ ባለቤትነት መብት አገኘ

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ አዕምሮዓዊ ንብረት ባለስልጣን ለሰባት ብሔራዊ የፈጠራ ግኝቶች የባለቤትነት መብት አግኝቷል።

እነኚህ የፈጠራ ውጤቶች ዩኒቨርሲቲው በመከላከያ የቴክኖሎጂ ፈጠራ እና በወታደራዊ ምርምር ውስጥ ግንባር ቀደም ተቋም መሆኑን የሚያጠናክሩ ናቸው።

የዩኒቨርሲቲው የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ኘሬዝዳንት ፅ/ቤት መረጃ እንደሚያመለክተው ይህ ስኬት ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ በሀገር ልጅ ወታደራዊ ቴክኖሎጂዎችን የማምረት አቅሟን በማጠናከር ከውጭ አቅራቢዎች ላይ ያላትን ጥገኝነት በእጅጉ ይቀንሳል።

የፈጠራ ውጤቶቹ የተገኙት በዩኒቨርሲቲው ባሉ ከፍተኛ ወታደራዊ ኢንጂነሮች ፣ የቴክኖሎጂ ላብራቶሪዎች እና የአካዳሚክ ተመራማሪዎች የተቀናጀ ጠንካራ የምርምር ስራ እንደሆነ ፅ/ቤቱ ጠቁሟል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተመዘገቡት ሰባቱ የፈጠራ ባለቤትነት መብቶችም በSmart Power Bag፣ በ122ሚሜ መድፍ የከሸፈ (የተቀረቀረ) ጥይት ማውጫ መሳሪያ ፣ በPick up -Mounted Rocket Pod System for Ground Forces ፣ በድሽቃ የተገጠመለትና ጥይት የማይበሳው ወታደራዊ ተሽከርካሪ ፣ በ155 ሚሜ መድፍ ውስጥ የከሸፈ(የተቀረቀረ) ጥይት ማውጫ ፣ የሪቨርስ ኢንጂነሪንግ ዘዴን በመጠቀም 120 ሚሜ ሞርታር መሳሪያ መስራት ፣ በ120 ሚሜ ሞርታር መኪና ላይ መጫን የሚሉት ናቸው።

በኢትዮጵያ አዕምሮዓዊ ንብረት ባለስልጣን የፈጠራ ባለቤትነት የምስክር ወረቀት መሠረት የፈጠራ ውጤቶቹ በኢትዮጵያ የአዕምሮ ንብረት ማዕቀፍ ውስጥ አዲስ ግኝት መሆናቸውን ፣ የፈጠራ ደረጃ እና የኢንዱስትሪ ህጋዊ ደረጃዎችን ማሟላታቸው ተረጋግጦ እውቅና የተሰጣቸው እንደሆኑም የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ኘሬዝዳንት ፅ/ቤት አስታውቋል።

የፈጠራ ባለቤትነት እውቅናውን ተከትሎ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ እያንዳንዳቸውን የፈጠራ ውጤቶች የማምረት ፣ የማሰራጨት ወይም ለአገልግሎት እንዲውሉ የመፈቀድ መብቶች እንዳሉት አረጋግጧል።

(ኢመዩ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...