የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት 3 ሺሕ አዳዲስ ማኅበራት ሊመሠርት ነዉ

Date:

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) በሀገሪቱ ያለውን የሠራተኛ ማኅበራት ምጣኔ ለማሳደግ ታስቦ በተያዘ ዕቅድ መሠረት፤ 3 ሺሕ የሚደርሱ አዳዲስ የሠራተኛ ማኅበራትን ለማደራጀት እየሠራ መሆኑን ገልጿል።

ኮንፌዴሬሽኑ ይህንን እርምጃ የወሰደው ሠራተኞች ሲደራጁ፤ አሠሪዎች ከሥራ የማባረርና ከደረጃ ዝቅ የማድረግ እንዲሁም መሰል ችግሮች በሀገሪቱ እየተስተዋሉ ባለበት ወቅት መሆኑን አስታውቋል።

የኢሰማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ እንደተናገሩት፤ ሠራተኞችን ከመንግሥት ጋር በመተባበር የማደራጀት ሥራ የሚካሄድ ሲሆን፤ ይህን ማድረግ ያስፈለገውም በሀገሪቱ የሠራተኛ ማኅበራት ምጣኔ አነስተኛ በመሆኑ ምክንያት ነው፡፡

ማኅበራቱ በየክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች በኩል የሠራተኞችን የማደራጀት ሥራ እንደሚካሄድ ገልጸው፤ ማኅበራት በሚደራጁበት ወቅት አሠሪዎች የሠራተኛ መብትን እንዲያከብሩ መንግሥት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ መሥራት እንዳለበት አሳስበዋል።

አቶ ካሳሁን አክለውም፤ የሠራተኞች መደራጀት ጨምሮ ሌሎች መብቶቻቸውን በማፈን የመብት ጥሰት የሚያደርሱ ኢንዱስትሪዎችን በቅርበት ለመከታተልና አፋጣኝ መፍትሔ ለመስጠት በማሰብ፤ በሁሉም ክልሎች በሚገኙ የኮንፌዴሬሽኑ ቅርንጫፎች በቅርበት የሚሰሩ ባለሙያዎች መሟላታቸውን አስታውቀዋል።

ተቋማት የፈጸሙት የመብት ጥሰት ሪፖርት በሚደረግበት ጊዜ በውይይት መፈታት ካልቻለ፤ ኮንፌዴሬሽኑ ወደ መደበኛው ፍርድ ቤት እንደሚያቀርበውም ተናግረዋል።

“ኢሰመኮ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ሠራተኞች ጋር ደርሶ እያንዳንዱን ድርጅት መጠየቅ አይችልም” ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ኮንፌዴሬሽኑ ተደጋጋሚ ቅሬታ የሚቀርብባቸውን ተቋማት በመለየት የቅርብ ክትትል እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።

የኮንፌዴሬሽኑ ቅርንጫፎች በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች የሚገኙ ሲሆን፤ እንደ ኮምቦልቻ፣ ባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ አዳማ፣ ጅማና ሻሸመኔ ባሉ ትላልቅ ኢንዱስትሪ መገኛ ከተሞች የበለጠ ትኩረት እንደሚደረግ አቶ ካሳሁን ገልጸዋል።

በተጨማሪም ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የመወሰን ሥራ አሁን ላይ ለሲቪል ሰርቪስ ሠራተኞች ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል መወሰኑን በማንሳት፤ ለግል ሠራተኞችም የደመወዝ ወለል ለመወሰን ሥራ መጀመሩን አስታውቋል።

ማኅበሩ ይህ የደመወዝ ደረጃ በፍጥነት ለግል ሠራተኞች ተግባራዊ እንዲደረግ እንደሚጥርም ተናግሯል።

የግል ሠራተኞችን ዝቅተኛ የደመወዝ ደረጃ የሚወስነው ቦርድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ ቁጥር እንደሚቋቋም ገልጸው፣ የቦርዱ ዋነኛ ሥራ ዝቅተኛ የደመወዝ ደረጃን መወሰን መሆኑን አብራርተዋል።

አቶ ካሳሁን ፎሎ በተጨማሪም፤ ይህ ቦርድ ሥራውን ሲያከናውን በጥናት ላይ የተመሠረተ ሥራ እንደሚሠራ እና ለግል ሠራተኞች ብቻ የተቋቋመ መሆኑን አውስተዋል።

የሚቋቋመው ቦርድ የመንግሥት የደሞዝ ደረጃን የማያወጣ መሆኑንም ጠቁመዋል፤ ይህ የሆነው የመንግሥት ሠራተኞች የደሞዝ ደረጃ ቀድሞ በመውጣቱ ምክንያት ነው።

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...