ጋዜጠኞችን ለቀናት ሰውረው ያቆዩ አካላት ወደ ሕግ ይቅረቡ

Date:

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር ጋዜጠኞችን ያሉበት በማይታወቅበት ሁኔታ ከ10 ቀናት በላይ ሰውረው ያቆዩ አካላት በግልፅ እንዲታወቁ እና በሕግ ፊት እንዲቀርቡ ጠየቀ።

ማህበሩ በአሀዱ ኤፍ ኤም 94.3 FM ሬዲዮ የቅዳሜ ገበያ ፕሮግራም አዘጋጅ  ጋዜጠኛ አብዱሰመድ ከ12 ቀናት በኋላ፤ የሪፖርተር ጋዜጣ ከፍተኛ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ዮናስ ደግሞ ከ10 ቀናት ስወራ ነጻ ወጥተው ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን ማረጋገጡን በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ ባሰፈረው ጽሑፉ አስታውቋል።

ጋዜጠኞቹ ያሉበት በማይታወቅበት ሁኔታ ከ10 ቀን በላይ ተሰውረው መቆየታቸው “ሕገ ወጥ ተግባር ነው” ያለው ማኅበሩ፤ የድርጊቱ ፈጻሚዎች በግልፅ ታውቀው በሕግ ፊት ተጠያቂ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር ይህን ያስታወቀው የሪፖርተር ጋዜጣ ከፍተኛ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ዮናስ አማረ እና በአሀዱ ኤፍ ኤም 94.3 FM ሬዲዮ የቅዳሜ ገበያ ፕሮግራም አዘጋጅ ጋዜጠኛ አብዱል ሰመድ መሀመድ እንደተለቀቁ መገለጹን ተከትሎ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...