ሙዚቃን ለንግድ አላማ የሚጠቀሙ ድርጅቶችና ተቋማት የ’ሮያሊቲ’ን ሕግ አለመረዳታቸው ክፍተት እየፈጠረ እንደሚገኝ ተገለጸ

Date:

የኢትዮጵያ ሙዚቀኞችን የሙዚቃ ሥራዎች ለንግድ አላማ የሚጠቀሙ ድርጅቶችና ተቋማት፤ የ’ሮያሊቲ’ን ሕግ አለመረዳታቸው ክፍተት እንደፈጠረበት የኢትዮጵያ የአዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ለአሐዱ አስታውቋል።

የቅጂና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ አዋጅ ማናቸውንም ወጥ እና ትርጉም የኪነ ጥበብ ሥራዎችን መዝግቦ ጥበቃ እንደሚያደርግላቸው የተናገሩት የባለስልጣኑ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኤልያስ መሀመድ ናቸው።

በቅጂ መብት ጥበቃ ላይ ደጋግመው ከሚያጋጥሙ ችግሮች መካከልም ሙዚቃን ገቢ ለሚያስገኝ ዓላማ የተጠቀሙ ድርጅቶች እና ግለሰቦች የ’ሮያሊቲ’ ክፍያ ለመፈጸም ፈቃደኛ አለመሆናቸው መሆኑን ለአሐዱ ተናግረዋል።

ኃላፊው አክለውም የሮያሊቲ ክፍያ በሌሎች ሀገራትም እየተሰራበት የሚገኝ ቢሆንም፤ በኢትዮጵያ ተግባራዊ እንዳይደረግ በዘርፉ ተዋንያን ዘንድ ሮያሊቲን የመረዳት ችግር እንዳለ አንስተዋል።

ማናቸውም ሙዚቃን ለንግድ አላማ ያዋለ ድርጅት ወይም ግለሰብ ለሥራው ባለቤቶች ክፍያ መፈጸም እንደሚገባው የሚደነግግ ሕግ ቢኖርም፤ “ተግባራዊ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ” ብለዋል።

ሚንስትር መስሪያ ቤቱ ከሥራዎቻቸው ተጠቃሚ ለመሆን ማኅበር ያቋቋሙ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችን በማገዝ ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

ኃላፊው እንደገለጹት ሮያሊቲ ክፍያን ለማስጀመር ለንግድ ተቋማት፣ ለመገናኛ ብዙኃን፣ ለጂጄዎች እና ለሌሎችም የማሳወቅ ሥራዎች በመሰራት ሲሆኑ፤ “ከምክክር ሂደቱ በኋላ ወደ ተግባራዊነቱ እንገባለን” ብለዋል።

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...

ከአሜሪካ ጋር የሚኖረው “የጨዋታው ሕግ ተቀይሯል፤ የተመጣጠነ ምላሽ ዘመን አብቅቷል

ኢራን ከአሜሪካ በኩል ለሚሰነዘርባት ጥቃት የምትሰጠው ተመጣጣኝ የአጸፋ ምላሽ...

የ2.5 ቢሊየን ብር ግዙፍ ፕሮጀክት በአታ ለማርያም ገዳም በመስከረም ወር የመሠረት ድንጋይ ሊያኖር ነዉ

​በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ የታዕካ ነገሥት...

የዲቪ ዕድለኞች የማመልከቻ ሂደታቸውን እንዲቀጥሉ ተወሰነ!

የአሜሪካ የፌዴራል ፍርድ ቤት በዲቪ ሎተሪ አመልካቾች የማመልከቻ ሂደት...