በሀረር 40 ቋሚ እና 100 ተንቀሳቃሽ ቅርሶች ተመዘገቡ

Date:

በሀረር ክልል በበጀት ዓመቱ 40 ቋሚ ቅርሶችን ለመመዝገብ በታቀደው መሰረት 40 በጀጎል ውስጥ የሚገኙ ባህላዊ ቋሚ ቅርሶችን ለመመዝገብ ተችሏል፡፡

በተጨማሪም 100 ተንቀሳቀሽ ቅርሶችን ለመመዝገብ በታቀደው መሰረት 100 በብሔራዊ ሙዚየም የሚገኙ የባህላዊ እቃዎች ለመመዝገብ መቻሉን የሀረሪ ክልል የባህል ቅርስ እና ቱሪዝም የእቅድ ዝግጅት ክትትል እና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አፈንዲ አብዲ ኡስማኤል ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ለተቋም አቅም ግንባታ በፌዴራልና በተለያዩ ድጋፍ እድራጊ ድርጅቶች ደረጃ የቁሳቁስ፣ የገንዘብ እና የስልጠና ድጋፍ 500ሺህ ብር የሚገመት ቁሳቁስ እና ሌሎች ድጋፎች ለማሳባሰብ ታቅዶ 700ሺህ ብር በላይ ቁሳቁስ እና ሌሎች ድጋፎች በማሰባሰብ 100 በመቶ እቅዱን ለማሳካት ተችላል።

በበጀት ዓመቱ ውስጥ በብልሹ አሰራር ዙሪያ የመጡ ጥቆማዎችን ለማስተካከል በታቀደው መሰረት የመጡ ጥቆማዎችን ትክክለኛነት ለማረጋገጥና ቦታቸው ድረስ በመሄድና መረጃዎችን በማሰባሰብና በማጣራት ትክክለኛ ውሳኔ እንዲተላለፍና የማስተካከያ ሥራ ሙሉ በሙሉ ተከናውኗል።

እንዲሁም በበጀት ዓመቱ ጎጂ ባህላዊ ልምድ በ10 በመቶ ለመቀነስ በታቀደው መሰረት ቢሮው ከሴቶች፣ህፃነት እና ወጣቶች እና ሌሎች ሴክተር መስራቤቶች ጋር በጋራ በመሆን በክልሉ አሉታዊ መጤ ልማዳዊ ድርጊቶች እና አደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚዎችን ቁጥር ለመቀነስ አላማ ያደረገ ስራ መሠራቱን ገልፀዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...