የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለሩሲያው አቻቸውን ቭላድሚር ፑቲን እና ቤላሩሱ አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ጥሪ አቀረቡ።
የጋዛን መልሶ ግንባታ በሚያስተባብረው የሰላም ጓድ (board of peace) ሩሲያ እና ቤላሩስ አባል በመሆን እንዲያግዙ ጥሪ ማቅረቡን የትራምፕ አስተዳደር አስታውቋል።
ጥሪውን አስመልክቶ አስተያየት የሰጡት የክሬምሊኑ ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ፣ ፑቲን ጉዳዩን እያጤኑት ነው ሲሉ ለመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች መግለጫ ሰጥተዋል ።
ፑቲን ጥሪውን እንደተቀበሉ የገለፁት ፔስኮቭ በዝርዝር ጉዳዮች ላይ ውይይት እየተደረገበት እንደሆነም አክለዋል።
የቤላሩስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ፣ ትራምፕ የላኩትን ደብዳቤ እንደተቀበለ ማረጋገጡን በኤክስ ገፁ ላይ አስፍሯል።
ትራምፕ ጋዛን መልሶ ለመገንባት በሚል የተለያዩ ሀገራትን ለማሳተፍ ጥሪ እያደረጉ መሆኑን ተከትሎ፣ ሩሲያ እና ቤላሩስ የሰላም ጓዱ መስራች አባል እንዲሆኑ ፍላጎት አሳይተዋል ተብሏል።
ትራምፕ የጋዛን ጉዳይ በበላይነት ራሳቸው እየመሩ፣ አስፈጻሚዎች ደግሞ ማርኮ ሩቢዮ እና የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌር እንዲሆኑ ሹመት መስጠታቸው ይታወሳል። ፎክስ ኒውስ እንደዘገበዉ።
