ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከ(CIFF) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጋር ተወያዩ

Date:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የቺልድረን ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን (CIFF) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኬቲ ሃምፕተን እና የሥራ ባልደረቦቻቸውን በዛሬው ዕለት በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ከንቲባዋ እና የፋውንዴሽኑ አመራሮች በጋራ በመሆን የ”ለነገዋ” የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከልን የጎበኙ ሲሆን፣ በማዕከሉ ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ የልማትና የድጋፍ ሥራዎችን ተመልክተዋል።

ከንቲባዋ እና ኬቲ ሃምፕተን በማዕከሉ የሚገኙ ሴቶች የሚያገኟቸውን የስልጠና እና የተሃድሶ አገልግሎቶች በቅርበት መርምረዋል። በጉብኝቱ ወቅት በቀጣይ በጋራ ሊሰሩባቸው በሚገቡ የትኩረት መስኮች ላይ ሰፊ ውይይት መደረጉን ከንቲባዋ ገልጸዋል።

ፋውንዴሽኑ በሴቶች አቅም ግንባታ እና በክህሎት ማበልፀጊያ ዘርፎች ላይ ያለውን አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር መግባባት ላይ ተደርሷል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ ውይይቱ እጅግ ውጤታማ እንደነበርና ለሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...