የአቶ አማን ፍስሐ ጽዮን ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ

Date:

በኢትዮጵያ የሚዲያ ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ የከፈቱት እና የኢቢኤስ ቴሌቪዥን መሥራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት የአቶ አማን ፍስሐ ጽዮን የቀብር ሥነ-ሥርዓት ሐሙስ የካቲት 12 2018 ዓ .ም ተፈጽሟል።

ቀደም ሲል በዓድዋ ድል መታሰቢያ በተከናወነው የክብር ሽኝት መርሐ-ግብር ላይ የቤተሰብ አባላት የአቶ አማንን መልካም አባትነት እና ለቤተሰባቸው የነበራቸውን ጥልቅ ፍቅር የሚዘክሩ ልብ የሚነኩ ንግግሮችን አድርገዋል።

የሃይማኖት አባቶች አቶ አማን በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ሁሉም እምነቶች በእኩልነት ለተከታዮቻቸው አስተምህሮታቸውን መንገድ የከፈተ ሚዲያ እንዲሆን ማስቻላቸውን መስክረዋል።

በተለይም በኮቪድ 19 ወቅት ከእምነት ተቋማት ጋር የሠሩት ሥራ ሲያስመሰግናቸው እንደሚኖር ነው የገለጹት።

ባለትዳር እና የሦስት ልጆች አባት የነበሩት አቶ አማን ፍስሐ ጽዮን ከቤተሰብ ኃላፊነታቸው ባሻገር፣ በሚሊዮኖች ዘንድ ተወዳጅ የሆነውን ኢቢኤስን በመመሥረት ለሀገራቸው ተወዳጅ የሚዲያ ውጤት ያበረከቱ ታታሪ መሪ እንደነበሩ ይመሰከርላቸዋል።

የአቶ አማን ፍስሐ ጽዮን ሥርዓተ ቀብር በአዲስ አበባ የቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ የሥራ ባልደረቦቻቸው እና በርካታ የጥበብ ሰዎች በተገኙበት ተፈጽሟል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...