የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ተጨማሪ ቦይንግ 787- 8 ድሪምላይነር አውሮፕላን በዛሬው ዕለት ተረክቧል፡፡
አዲሱ አውሮፕላን በአንድ ጊዜ 213 መንገደኞችን የሚያጓጉዝ ሲሆን ÷ የሚሰጠውን ምቹና ጥራት ያለው አገልግሎት እንደሚያጠናክርም ተመላክቷል፡፡
አሁን ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተረከባቸው ቦይንግ 787- 8 ድሪምላይነር አውሮፕላኖች ቁጥር 30 መድረሱንም አየር መንገዱ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡
