ማንችስተር ሲቲ በአል ሂላል ተሸነፈ

Date:

ማራኪ እንቅስቃሴ በተስተዋለበት ጨዋታ የሳዑዲ አረቢያው ክለብ 4 ለ3 በማሸነፍ የሩብ ፍጻሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋጧል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች መደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜውን ሁለት አቻ ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ አሸናፊውን ለመለየት ወደ ጭማሬ 30 ደቂቃ አምርተዋል፡፡

በካምፒንግ ዎርልድ ስቴዲየም በተደረገው ጨዋታ ማርከስ ሊዮናርዶ ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል፡፡ 

ማልኮም እና ካሊሊዱ ኩሊባሊ ደግሞ ቀሪዎቹን ግቦች ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

በርናዶ ሲልቫ፣ እርሊንግ ሃላንድ እና ፊል ፎደን የማንችስተር ሲቲን ግቦች አስቆጥረዋል፡፡

በቅርቡ ከኢንተር ሚላን ጋር ከተለያየ በኋላ ወደ ሳዑዲ አረቢያው ክለብ ያመራው ሲሞን ኢንዛጊ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ በማችስተር ሲቲ ተሸንፎ ዋንጫውን ማጣቱም ይታወሳል፡፡

የሲሞን ኢንዛጊው ቡድን አል ሂላል በሩብ ፍጻሜው ከብራዚሉ ፍሉሚነንስ የሚጫወት ይሆናል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...