ራይድ ከቦሰተን ፓርትነርስ ጋር የስራ ስምምነት ተፈራረመ

Date:

ራይድ ትራንስፖርት ከቦስተን ፓረተነርስ ጋር ዓለም አቀፍ ይዘቱን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት በሚችልበት ሁኔታ በጋራ ለመስራት የስራ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ሁለቱ ተቋማት ግዙፍ አገልገሎት አቅራቢዎች እንደመሆናቸው መጠን በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል፡፡ በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የራይድ ትራንስፖርት ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሳምራዊት ፍቅሩ ራይድ ትራስፖርት በአገራችን የዲጂታል ትራንስፖርት አገልግሎት ፈር – ቀዳጅ እንደሆነ ገልፀው፣ ሰዎችን ከዕድሎች ጋር በማገኛኘት የዕለት ተዕለት የኑሮ ዘይቤያቸው የተሻለ እንዲሆን መስራት የተመሰረተበት ራዕይ መሆኑ አስረድተዋል ፡፡

ሰለሆነም ይህንን ራዕይ ለማሳካት ከተለያ አገር-አቀፍ እና ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ጋር በትብብር እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው ከቦስተን ፓርትነርስ ጋር እያደረግን ያለነው ይህንኑ ዓላማችንን የበለጠ ለማሳለጥ ነው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል የቦስተን ፓረተነርስ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታዲዎስ ጌታቸው ድርጅታቸው ላለፉት 24 ዓመታት አዳዲስ የቱሪዝም አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ ሲያቀርብ የቆየ ተቋም መሆኑን ተናግረው በተለያዩ ከተሞች አገልግሎቶቹን እያሰፋ ይገኛል ብለዋል፡፡

ከራይድ ጋር በምናደርገው ስምምነትም፡-
1ኛ እንደ እንጦጦ ፓርክ፣ አፍሪካ ቪሌጅ ፣ ኩሪፍቱ ቢሾፍቱ ሪዞርቶች ራይድ የኤሌክትሪክ መኪኖችን በመመደብ ከቦስተን ፓረተነርስ ጋር በጋራ ይሰራል፣

2ኛ በኩሪፍቱ ሪዞርቶች በሚካሄዱ ትልልቅ ስብሰባዎች፣የጋብቻ ስነ-ስርዓቶች እና ኮንሰርቶች በሚዘጋጁበት ወቅት ራይድ ትራንስፖርት በቂ እና አስተማማኝ ትራንስፖርት ያቀርባል፣

3ኛ የራይድ ትራንስፖርትንም ሆነ የቦስተን ፓርትነርስን አገልግሎቶችን መልካም ስም እና ዝና በጠበቀ መልኩ የጋራ የገበያ ትስስር፣ የማስተዋወቅ እና የብራንድ ፕሮሞሽን ስራዎችን በትብብር ይሰራሉ፣

4ኛ ራይድ ትራንስፖርት አግልግሎት ለኩርፍቱ ሪዞርት ÷ ለቦስተን ስፓ ደንበኞች ያለምንም እንግልት በሚንቀሳቅሱበት የቱሪስት መስህብ ዘመናዊ ትራንስፖርት ያቀርባል፣

5ኛ አዳዲስ የገበያ ተደራሽነትን የሚያሰፉ ፓኬጆችን በጋራ በማዘጋጀት ለተጠቃዎች ለማድረስ በጋራ እንስራለን ሲሉ በስምምነቱ ላይ ተናግረዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...