የአንድ መንደር ሙሉ ነዋሪዎችን ህይወት የቀጠፈው የመሬት መንሸራተት አደጋ

Date:



በሱዳን ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት አደጋ 1000 ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ ። በሱዳን ምዕራባዊ ክፍል በሚገኘው ማራ ተራራ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ቢያንስ 1,000 ሰዎች መሞታቸውን የሱዳን ነፃነት ንቅናቄ ሠራዊት አስታውቋል።

በአከባቢው ለበርካታ ተከታታይ ቀናት የጣለው ከባድ ዝናብ የመሬት መንሸራተት ያስከተለ ሲሆን አንድ በአከባቢው የሚገኝ መንደር ሙሉ በሙሉ እንዲወድም አድርጓል።

የሱዳን ነፃነት ንቅናቄ ሠራዊት ባወጣው መግለጫ፣ ከአንድ ሰው በስተቀር በትራሲን  መንደር ውስጥ የነበሩ ሰዎች ሁሉ መሞታቸውን አስታውቋል።

በዚህ አስከፊና አደገኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ የትራሲን መንደር ሙሉ ለሙሉ በሚያስብል ደረጃ መውደሙ ነው የተነገረው።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ሌሎች ክልላዊ እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በማራ ተራራ አደጋ ለደረሰባቸው ተጎጂዎች አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታ እንዲያደርጉ አማጺው ቡድን ጥሪውን አቅርቧል።

በሱዳን ጦር እና በፓራሚሊታሪው ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች (RSF) መካከል በተፈጠረው ግጭት በርካታ የሰሜን ዳርፉር ግዛት ነዋሪዎች ተፈናቅለው በማራ ተራሮች ውስጥ ተጠልለው  እንደነበር ተገልጿል።

ዘገባው የቢቢሲ ነው

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...