ታግተው የነበሩ 25 ኢትዮጵያዊያን ተለቀቁ

Date:

በየመን በኢትዮጵያዊያን ታግተው የነበሩ 25 ኢትዮጵያዊያን ተለቀቁ፡፡ ሳውዝ 24 የተሰኘው የየመን ሚዲያ እንደገለፀው እነዚህ ኢትዮጵያዊያን በሻብዋ ግዛት ውስጥ ታግተው የነበሩ ናቸው፡፡

የሻብዋ ግዛት ዋና ከተማ በሆነው አታቅ ምስራቃዊ ክፍል የአገራቸው ልጆች በሆኑ በኢትዮጵያዊያን ከታገቱ በኋላ ቤተሰቦቻቸው የማስቀቂያ ገንዘብ እንዲከፍሉ መጠየቃቸውንም አስረድቷል፡፡ ይህ መረጃ የደረሰው የሻብዋ ፖሊስ ባደረገው ክትትል ታጋቾቹ ያሉበትን ቦታ ከደረሰበት በኋላ በወሰደው እርምጃ 25ቱንም ኢትዮጵያዊያን ትላንት ምሽት ማስለቀቅ መቻሉንም አስታውቋል፡፡

እንደፖሊስ መግለጫ በአጋቾቹ ቤት ውስጥ ከታገቱት ከእነዚህ ኢትዮጵያዊያን በተጨማሪ 15 ሚሊዮን የየመን ሪያልና 55 ሺህ የሳኡዲ ሪያል ተገኝቷል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...