ሂልተን ሆቴልን ጨምሮ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ስር የሚተዳደሩ አራት የቱሪዝም ዘርፍ ድርጅቶች፣ በ2017 የበጀት ዓመት ከታክስ በፊት 564.2 ሚሊዮን ብር ትርፍ ማግኘታቸው ተገለጸ። ይህ ውጤት ከታቀደው የትርፍ ግብ በ37 በመቶ ብልጫ ያለው መሆኑ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ባደረገዉ የስራ አፈጻጸም ግምገማ ፣ የስፓ አገልግሎት ኢንተርፕራይዝ (ፍል ዉሃ)፣ የጊዮን ሆቴሎች ኢንተርፕራይዝ፣ ሂልተን ሆቴል እና የገነት ሆቴልን ያካተተውን የሆቴል ዘርፍ አፈጻጸም ላይ ትኩረት አድርጓል።
ድርጅቶቹ በድምሩ 2.1 ቢሊዮን ብር ገቢ በማሰባሰብ ከታለመው 114 በመቶ ማሳካት ችለዋል የተባለ ሲሆን አሁን ላይ እያደገ የመጣውን የገበያ ፍላጎት እና የቱሪስቶች ፍሰት በመጠቀም ንግዳቸውን እንዲያሰፉ አሳስቧል።
ለዘላቂ እድገት ሲባልም የደንበኞችን እርካታ ማሻሻል፣ ዘመናዊ የግብይት ስልቶችን መጠቀም፣ እንዲሁም ዲጂታል አገልግሎትና የቦታ ማስያዣ ስርዓቶችን ማዘመን እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ተሰጥቷል።
CapitalNews
