የአፍሪካ አገራት እርስ በእርስ ያላቸው የንግድ ልውውጥ 15 በመቶ ብቻ ነዉ

Date:

በአፍሪካ አገራት መካከል ያለው የንግድ ትስስር አሁንም ዝቅተኛ መሆኑንና ይህም ከአህጉሪቱ ጠቅላላ የንግድ ልውውጥ 15 በመቶ ብቻ እንደሚሸፍን ተገለጸ። ይህ የተገለጸው በአዲስ አበባ በተካሄደውና የአፍሪካን የኢንዱስትሪ ሽግግር ለማፋጠን ያለመ ከፍተኛ የጎንዮሽ መድረክ ላይ ነው።

ይህ አሃዝ ከሌሎች የዓለም ክፍሎች ጋር ሲነጻጸር እጅግ ዝቅተኛ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም ለአፍሪካ የኢንዱስትሪ እድገት እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ትልቅ ማነቆ መሆኑ ተመልክቷል።

በተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት መፍትሄዎች መረብ (SDSN) ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመተባበር ባዘጋጁት በዚህ መድረክ ላይ ከፍተኛ የፖሊሲ አውጪዎች፣ የንግድ መሪዎች እና የልማት አጋሮች ተገኝተዋል።

በተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት መፍትሄዎች መረብ (SDSN) ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጄፍሪ ሳክስ በጉዳዩ ላይ እንደተናገሩት፣ አፍሪካ ያላትን የንፁህ ኢነርጂ ክምችት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠናን በመጠቀም ይህንን አሃዝ መቀየር እንደሚገባ አሳስበዋል።

አሁን የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት ቢኖርም፣ የአህጉሪቱ የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ ከሌሎች ቀጠናዎች (ለምሳሌ እንደ አውሮፓና እስያ) ጋር ሲነፃፀር እጅግ አናሳ መሆኑ ተመልክቷል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ባለሙያዎች የአፍሪካን የንግድ ልውውጥ ለማሳደግ የደቡብ-ደቡብ ትብብር በአፍሪካ አገራትና በሌሎች በማደግ ላይ ባሉ አገራት መካከል ያለውን የቴክኖሎጂና የኢኮኖሚ ትብብር ማጠናከር እና የኃይል አቅርቦትን ለማረጋገጥና ምርታማነትን ለመጨመር ዘመናዊና አካባቢን የማይበክሉ ቴክኖሎጂዎችን ማስፋፋት እንደሚያስፈልግ አፅንኦት በመስጠት ተናግረዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...