ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከ14 ሺህ ኪ.ግ በላይ ዓሳ በየቀኑ እየተመረተ እንደሆነ ተገለፀ

Date:

በግድቡ ከፍተኛ ተፈላጊነት ያላቸው የዓሳ ዝርያዎች እንደሚገኙና በቀን ከ14 ሺህ 500 ኪሎ ግራም በላይ ዓሳ እየተመረተ እንደሆነ ተገልጿል።

በግብርና ሚኒስቴር የዓሳ ልማት ዴስክ ኃላፊ ፋሲል ዳዊት ዘርፉ ከኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ባለፈ ለሥራ እድል ፈጠራ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው ማለታቸውን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

በግድቡ በጣም ተፈላጊ የሆነው ናይል ፐርች እንዲሁም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ተወዳጅ የሆነው ቀረሶ የዓሳ ዝርያ በስፋት እንደሚገኝ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

በታላቁ ህዳሴ ግድብ የዓሳ ምርት ዙሪያ 64 ማኅበራት እንደተደራጁ እና 23ቱ ማኅበራት ከውዲሁ የሥራ እድል መፍጠር እንደጀመሩም በዘገባው ተመላክቷል።

@sputnik_ethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...