የሕዳሴ ግድብን የተመለከተ የሰነድ ማስረጃ ያለው እንዲያቀርብ ተጠየቀ

Date:

የሕዳሴ ግድብን የተመለከተ የምስል፣ የጽሑፍ፣ የቪዲዮና መሰል ሰነዶች ያለው ማንኛውም ግለሰብ፤ ወደ ግድቡ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የፐብሊክ ዲፕሎማሲ የሕዝብ ግንኙነት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ እንዲያቀርብ ተጠይቋል፡፡   

በፕሮጀክቱ የማስተባበሪያ ጽፈት ቤት የፐብሊክ ዲፕሎማሲ የህዝብ ግንኙነት የኮሙኬሽን ኃላፊ አቶ ሰለሞን ዳንኤል ለአሐዱ እንደተናገሩት፤ የሰነድ ማስረጃዎቹ የተፈለጉት የግድቡን ሂደት እና ታሪካዊ ሁነቶችን የሚያሳዩ ማስረጃዎች ለዕይታ ለሚቀረቡበት ሙዚየም እንዲያገለግሉ ነው፡፡

እንደ ግብፅ ያሉ ሀገራት በሕዳሴው ግድብ ላይ የሚያሰራጩትን የሃሰት መረጃ ለመከላከል እንዲህ ዓይነት በማስረጃ ላይ የተመሠረቱ ዶክመንቶችን መሰብሰብ አስፈላጊ መሆኑንም ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡

“ሕዳሴው ግድብ በጠላት ፕሮፓጋንዳ የማይቀለበስበት ደረጃ ላይ ደርሷል” ያሉት ኃላፊው፤ የግድቡ ሙሌት ከ98 በመቶ በላይ መድረሱ ተናግረዋል፡፡

(አሐዱ ሬድዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ካናዳ ምዝገባም ሆነ ስምሪት አልተጀመረም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል"...

የክቡር ዶክተር ጋሽ መሐሙድ አዲስ አልበም ለአድማጮች ሊደርስ ነዉ

ታዋቂው ድምፃዊ ክቡር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አሕመድ «ለታሪክ» የተሰኘውንና...

ሜታ ‘ፌስቡክ እና ኢንስታግራም በቀረበባቸው ክስ 18 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ

ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ሜታ በፌስቡክ እና በኢንስታግራም ምክንያት...