የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ዛሬ እና ነገ ይካሄዳል

Date:

48ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ዛሬ እና ነገ በይካሄዳል

“ዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ስርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ በሚካሄደው ስብሰባ የሚሳተፉ የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ እየገቡ ነው።

በዚህም የሶማሊያ፣ የሴራሊዮን፣ የሳህራዊ ዲሞክራቲክ ዐረብ ሪፐብሊክ እና የሞሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

እንዲሁም የናይጀሪያ፣ የማላዊ፣ የኮትዲቯር፣ የቡሩንዲ፣ የኮንጎ ሪፐብሊክና የዛምቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል።

የሚኒስትሮች የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው ለ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ አጀንዳዎችን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

በስብሰባው ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞቿን በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ላይ በንቃት ለመሳተፍ መዘጋጀቷ ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...