* በባህር ዳርቻው ላይ አረፈ&
በምድራችን ከሚከሰቱ አደጋዎች የመትረፍ እድል እጅግ ጠባብ ከሆነባቸው የአውሮፕላን አደጋዎች መካከል፤ በጎረቤት ሀገር ሶማሊያ የተሰማው ዜና & ተብሏል።
የአደጋው ዝርዝር:
በስታርስኪ ኤቪዬሽን (Starsky Aviation) የሚንቀሳቀሰው እና Fokker 50 የተባለው የጭነትና የተሳፋሪ አውሮፕላን፤ ከሞቃዲሾ አደን አዴ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ እንደተነሳ የቴክኒክ ችግር አጋጥሞታል።
የፓይለቱ ጥረት:
አብራሪው አውሮፕላኑን ወደ ማረፊያ ጣቢያው ለመመለስ ቢሞክርም ሳይሳካለት ቀርቶ፤ ከማረፊያ መስመሩ (Runway) ወጥቶ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው የህንድ ውቅያኖስ ጥልቀት የሌለው የባህር ዳርቻ (Jasiira Beach) ላይ በሆዱ አርፏል።
ውጤቱ:
በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ 55 ተሳፋሪዎች እና የበረራ ባለሙያዎችን ህይወት ማትረፍ ተችሏል። በአደጋው ህይወቱ ያለፈ ሰው የሌለ ሲሆን ጥቂት ሰዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ዘ ሚረር / ኤርላይቭ
