የኤሌትሪክ ተሽከርካሪዎች አምራች እና አከፋፋይ ዶዳይ ማኑፋክቸሪንግ  ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ  ጋር አብሬ መስራት ጀመርኩ አለ

Date:


ዶዳይ የሐገሪቱን የኤሌትሪክ ትራንስፖርት አጀንዳ ለመደገፍ ባለኝ ቁርጠኝነት 40  የኤሌክትሪክ   ሞተሮች  ለአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ሰጥቻለሁ ብሏል።

የተበረከቱት ኤሌክትሪክ -ሞተር ሳይክሎች ከዶዳይ ዘመናዊ የባትሪ መለዋወጫ አውታር ጋር ሙሉ ለሙሉ የተገናኙ ሲሆኑ  ከዶዳይ ስማርት ኔትወርክ ጋር የተገናኙ በመሆናቸው፤ አሸክርካሪዎች በስልካቸው ክፍያ እንዲከፍሉ እና ሃይል ያለቀበትን ባትሪያቸውን በ5 ደቂቃ ወዲያውኑ ሙሉ በሙሉ ቻርጅ ባረገ ባትሪ እንዲቀበሉ ያስችላቸዋል ተብሏል ።

ኩባንያው ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ጋር ያደረገው ስትራቴጂካዊ ትስስር የከተማ ትራንስፖርትን ለማሳደግ፣ የኤሌትሪክ ተሽከርካሪ ዘላቂነት ለማስተዋወቅ እና ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች አዲስ የስራ እድሎችን ለመፍጠር ያለመ ነው መሆኑ ተጠቅሷል።

የዶዳይ ማኑፋክቸሪንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዩማ ሳሳኪ ” ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ እና ከወሳኝ የከተማ ተቋማት ጋር በመተባበር ስራ በመጀመራችን ደስታ ይሰማናል” ሲሉ መናገራቸው ተሰምቷል ።

የጃፓኑ ዶዳይ ኩባንያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች አምራችና አከፋፋይ  ሲሆን አዳዲስ እና ዘላቂ የትራንስፖርት መፍትሄዎችን ለማቅረብ ቁርጠኛ ነኝ ብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...