150 ሰዎችን አውጥተን ቤቶቹን አሽገናል

Date:

በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ መጠሪያው ሚኪሊላንድ ኮንዶሚኒየም በተባለ አካባቢ የመሬት መንሸራት አደጋ ማጋጠሙ፣ ድልድይ በመደርመሱ ነዋሪዎችም ከቤታቸው እንዲወጡ ተደርጓል።

ስለአደጋው ለኤኤምኤን ማብራሪያ የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጂ ኢ/ር ወንድሙ ሴታ፣ “ አደጋው ሚኪሊላንድ ኮንደቀሚኒየም ብሎክ 13 ጋ ብቻ አይደለም። ከሚኪሊላንድ የመጀመሪያ ደረጃና መካከለኛ ት/ቤት አጥርም በተመሳሳይ መልኩ ጉዳት የደረሰበት ሁኔታ አለ ” ብለዋል።

በሌላ ቦታ ወረዳ 14 አንድ ቤተ እምነት ግቢ ውስጥ ያለ የዋዕለ ህፃናትና መጸዳጃ ቤት ላይ የደረሰ ተመሳሳይ ጉዳት መኖሩንም አክለዋል።

“ ይሄ ጉዳት ምልክት ማሳየት የጀመረው ነሐሴ 15 ቀን 2017 ዓ/ም አካባቢ ነው። በኮንዶሚኒየሙ ባለው ጀርባ መንገድ ላይ ስንጥቅ መታየት ነበር የጀመረው ” ሲሉም የሁነቱን መነሻ አስረድተዋል።

“ ሲጀምር የመሬት መሰንጠቅ ነው የነበረው በኋላ ላይ ግን በተለይ ከነሐሴ አጋማሽ ወዲህ ባለው ከፍተኛ የሆነ ዝናብ አፈሩ በጣም ከፍተኛ የውሃ መጠን በሚይዝበት ጊዜ ልል በመሆኑ ወደ መስመጥ፣ የታችኛው የወንዙ ክፍል ደግሞ የመሸርሸር አደጋ እንደደረሰ አይተናል ” ነው ያሉት።

ኢ/ር ወንድሙ መንስኤው በተመለከተ ምን አሉ ?

“ እዛ አካባቢ ያለው ወንዝ ከፍተኛ ተዳፋት የነበረ ቦታ ነው፤ የሚነሳበትንም ቦታ ከጉለሌ ቦታኒካል ጋርደን ጀምሮ ካሽመንት እየሰበሰበ የሚመጣ ነው። የሚኪሊላንድ ኮንዶሚኒየም በሚሰራበት ጊዜ ወደ 123 ፍሎር የሚጠጋ ነው።

አብዛኛው ከዛ ይወጣ የነበረው የተቆፈረ አፈር ምልስ የነበረበት፣ መንገዱም ሲሰራ ያንን ታሳቢ ያላደረገ፣ ከአካባቢው የሚመጣው ውሃ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ምክንያት ያ የመሬት መሰንጠቅ ወደ መሬት መስመጥ፣ በታችኛው የወንዝ ተፋሰስ ክፍልም መንሸራተት አምጥቷል።

ሳይቱ ወደ 123 ብሎኮች አሉት፤ ወደ 4272 የሚጠጉ አባውራዎች የሚኖሩበት አካባቢ ነው። ከዚህ ሁሉ ቦታ ከህንፃ ላይ የሚወርደው የዝናብ ውሃ ወደ ወንዝ መሄድ መቻል አለበት።

በኮንዶሚኒየሞቹ ዙሪያ ያሉ የጎርፍ ማፋሰሻ ቱቦዎች በተለያዬ ቆሻሻ የተደፈኑ በመሆናቸው ውሃው ወደ ወንዙ አይሄድም፤ እዛው ነው የሚሰርገው። እንዲሁም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ከ8 እስከ 12 ሜትር የሚሆን አዲስ ምልስ አፈር በዛ አካባቢ እንዳለ ነው ያሳየን ” ብለዋል፡፡

ለነዋሪዎቹ የቅድመ ጥንቃቄ ሥራ ስለመስራት ተጠይቀው ምን መለሱ ?

በነዋሪዎቹ ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ምን የቅድመ ጥንቃቄ ስራ እየተሰራ እንደሆነ ሲጠየቁ፣ “ ምልክት ከታዮበት ጊዜ ጀምሮ በአካባቢው ከሚኖሩ ሰዎች፣ ባጠገቡ ካለው ት/ቤት ጋር ውይይት አድርገን በተለይም ብሎክ 13 ስሰነበረ የበለጠ ተጋላጭ የነበረው በጊዜያዊነት ከቤት እንዲወጡና እንደዲታሸግ ተደርጓል ” ብለዋል።

በቦታው የሰዎችና የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እንዳይኖር የመከልከል ሥራ መሰራቱንም፣ ምሁራን አቀረቡት ባሉት ሪፓርት መሰረት የማቅለያ ሥራ ለመስራት መታቀዱንም ጠቁመዋል።

ኢ/ር ወንድሙ፣ “ አጠገቡ ያሉ መንገዶች በመደርመሳቸው ለአደጋ ተጋላጫነታቸው ስለሚጨምር በአንድ ብሎክ ውስጥ የሚኖሩ ወደ 150 ሰዎችን አውጥተናል። ቤቶቹንም አሽገናል” ሲሉምተናግረዋል፡፡

ዘላቂ መፈትሄ የሚሆነው ወንዙን ከላይኛው ተፋሰስ ጀምሮ በእርከን የማስተካከልና ከሰው እንቅስቃሴ የጸዳ ማድረግ መሆኑን፣ ይህ ካልተሰራ የአደጋ ስጋቱ በጣም በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ እንደሚሄድ ምክረ ሀሳብ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ምሁራን መገኘነቱን አስረድተዋል ሲል ቲክቫህ ዘግቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...