
የአ/አ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ማስጠንቀቂያ ሰጠ
የአዲስ አበባ መጅሊስ ከዚህ በኋላ በመስጂዶች ጉዳይ አይታገስም።
በአብዛኛዎቹ መስጂዶች ህዝበ ሙሰሊሙ እምነቱ በሚያዘው መሠረት ዒባዳውን እያከናወነ ሲሆን በጣት በሚቆጠሩ መስጂዶች ሁከት ለማስነሣት የተደረጉ ሙከራዎችን በየመሰጂዱ የሚገኙ ኮሚቴዎች፣ ሀዲሞችና ህብረተሰቡ ባደረገው ጥረት በቁጥጥር ሰር ሊውሉ ችሏል።
በተለይም ጠሮ መስጂድ ፣ሎሚ ሜዳ(ዓሊ) መስጂድና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 የሚገኘው ሀምዛ መሰጂድ የረመዳንን መግባት ተከትሎ በአንዳንድ ሰውር አላማ ያላቸው ግለሰቦች ሁከትና ብጥብጥ በማሰነሣት ከፍተኛ ችግር ሲፈጥሩ የቆዩ አካላት መሸሸጊያ ሆኖ የቆየ ቢሆንም መጅሊስ ከዛሬ ነገ ይቀየራሉ ብሎ ሁኔታውን አባታዊ በሆነ ትዕግሰት ይዞት ቆይቷል።
መጅሊሰ በእነዚህ ጥቂት መስጂዶች የተፈጠሩትን ችግሮች ለመፍታት የተለያዩ ጥረቶችን ቢያደርግም ዕድሉን ባለመጠቀም ቡድኑ መሰጂድ ሰብሮ በመግባት፣ ጄነሬተር በማጥፋት፣ ለደህንነት የተገጠመ ካሜራን በመሰባበር እና አማኞች የተረጋጋ ዒባዳ(የአምልኮ ስርዓት) እንዳይከውኑና የረመዳንን ወር የብጥብጥና የረብሻ አውድማ የማድረግ እንቅሰቃሴያቸውን ቀጥለውበታል።
ከወራት በፊት ማዕከላቸውንና የብጥብጥ መነሻቸውን ዓሊ መስጂድ በማድረግ ሴቶችና ህፃናትን ከፊት በማሰለፍና የተወሰኑ ግለሰቦች እያወናበዱ ይገኛሉ።