ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ 170 ቦታዎችን ተሠሩ

Date:

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን በመለያት የተለያዩ ስራዎች ማከናወኑን አስታወቀ ።

በአዲስ አበባ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ 170 ቦታዎችን በመለየት ግንባታው ሰርቶ ያጠናቀቀ መሆኑን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ምክትል ኃላፊ አቶ እያሱ ሰለሞን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

ከደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻዎች አያያዝና አወጋገድ፣ እንዲሁም በግንባታ ግብዓትና ተረፈ-ምርት ማጓጓዝ ሂደት በድሬኔጅ መስመሮች ላይ በሚፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎል ሳቢያ በከተማዋ ጎዳናዎች ላይ በተደጋጋሚ የሚከሰተው ጎርፍ የትራፊክ እንቅስቃሴውን እያስተጓጎለው ይገኛል ተብሏል።

ይህንን ችግር ለመፍታት ባለስልጣን መሰሪቤቱ ባለፉት ወራቶችየመንገድ ዳር የወሃ መፋሰሻ መስመሮች ጽዳትና ጥገና ሥራ አከናውኗል፡፡ባለሥልጣን መሰሪያቤቱ ከዚህም በተጨማሪም ከእሳት እና አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን የሚላኩ ጥቆማዎችን ጨምሮ የጎርፍ አደጋ ስጋት ያለባቸውን ሥፍራዎች አካቶ የማስተካከያ ሥራዎች በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በቀጣይም ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ 30 ቦታዎች በመለየት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ስራዎች እንደሚከናወኑ አቶ እያሱ ሰለሞን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...