በጋብቻ ላይ ጋብቻ የመፈጸም ልማድን ማስቀረት አልተቻለም 

Date:

በጋብቻ ላይ ተጨማሪ ጋብቻን የመፈፀም ድርጊትን ለማስቀረት የተለያዩ ሥራዎች ቢሰራም ችግሩን አሁንም ድረስ መቅረፍ እንዳልተቻለ የጋምቤላ ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል።

አንድ ወንድ ሦስትና አራት ሴቶችን የሚያገባበት ልማድ መኖሩን ያነሱት በቢሮው የሴቶችና ሕጻናት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ኦላንግ ጋች፤ ይህ ድርጊትም ሴቶች የሚቸገሩበት ጉዳይ ስለመሆኑ ገልጸዋል።

በክልሉ ይህንና ሌሎች ጎጂ ልማዳዊ የሆኑ ድርጊቶችን ለማስቀረት የተጠናከረ ሥራ እንደሚሰራ አንስተው፤ ለውጥ እየታየባቸው ያሉ አንዳንድ ጉዳዮች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡

ለአብነትም ያለ ዕድሜ ጋብቻ በብዛት የሚስተዋል እንደነበረ አስታውሰው፤ ለልጆች በየትምህርት ቤቱ ስልጠና በመስጠትና  የሐይማኖት አባቶችንም በማስተባበር ወላጆች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ በመሰራቱ ቀድሞ ከነበረበት እየቀነሰ ስለመምጣቱ አስታውቀዋል።

ነገር ግን አንድ ወንድ ከአንዲት ሴት በላይ የሚያገባበትን ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ለማስቀረት በተሰራው ሥራ የሚፈለገውን ያህል ለውጥ አለመምጣቱን ተናግረዋል፡፡

ማህበረሰቡን ከማስተማር ባለፈ በአመራር ደረጃ ያሉት ሰዎችን ድርጊቱን እንዳይፈፅሙ በመከልከል ለማስቀረት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...