- የባንኩ የብድር አገልግሎቱ ለኢንቨስትመንት፣ ለመኖሪያ ቤትና አውቶሞቢል ግዥ የቀረበ ነው ተብሏል፣
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚደንት አቶ አቤ ሳኖ ሰሞኑን በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ ወቅት ፕሬዚደንቱ እንዳስታወቁት ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በአገር ውስጥ ለሚያካሄዱት የቢዝነስ እንቅስቃሴ፣ ለመኖሪያ ቤትና መሰል ፍላጎቶች የ50 ቢሊዮን ብር የብድር አገልገሎት ተመቻችቷል፡፡
የብድር አገልግሎቱ በተያዘው የበጀት ዓመት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
ባንካችን አገልግሎቱን ለማግኘት ጥያቄ ለሚያቀርቡ የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ቀልጣፋና ምቹ አሰራር እንደሚተገብርም አቶ አቤ አስታውቀዋል፡፡
(ኢንባ)
