በአዲስ አበባ፣ ጋምቤላ እና ሐረሪ ከፍተኛ የኤች አይ ቪ ስርጭት ባለባቸው ክልሎች ቀዳሚውን ስፍራ ይዘዋል ነው የተባለው።
መረጃው የወጣው በኤች አይ ቪ እና ቲቢ በሽታዎች ላይ በሚሰራው ኤድስ ሄልዝኬር ፋውንዴሽን ነው።
በየዓመቱ ወደ 8 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ እንደሚያዙ ተቋሙ ገልጿል።
በአጠቃላይ ከ600 ሺህ በላይ ሰዎች ከቫይረሱ ጋር ሲኖሩ ከእነዚህ ውስጥ 64 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው ተብሏል።
ምንም እንኳን በ2010 ዓ.ም ከነበረው 1 ነጥብ 6 በመቶ የስርጭት መጠን በ2024 ወደ 0 ነጥብ 85 በመቶ ቢቀንስም እንደየህብረተሰብ ክፍሎች አይነት፣ የሥራ ዘርፍ መጠኑ ሊጨምር እንደሚችል ነው የተጠቆመው።
እንደ የረጅም ርቀት አሽከርካሪዎች፣ የኢንዱስትሪ ሠራተኞች እና ወጣት ሴቶች ያሉ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ትኩረት የሚሹ እንደሆኑም ተነስቷል።
የኤድስ ሄልዝኬር ፋውንዴሽን የኤች አይ ቪ ስርጭትን ለመቀነስ የቅስቀሳ ሥራዎች፣ ኮንዶም በአግባቡ መጠቀም፣ መደበኛ ምርመራዎች እና ተጋላጭ የሆኑ ሴቶችን በኢኮኖሚ መደገፍ ወሳኝ መፍትሄዎች መሆናቸውን አሳስቧል።
