የቴዲ አፍሮ አድናቂ ነኝ።
እንደ አንድ ኢትዮጵያኒስት እና የአፍሪቃ ብሄርተኛ ከብላቴናው በላይ ተስማሚ ዘፋኝ የለኝም።
ብዙ የሚኮረኩሩኝ፣ የሚኳሹኝ እና ድንበር ዘለል ምናበኛ የሚያደርጉኝ ስራዎች አሉት። ቴዲ ከብሄርብሄረሰቡ እና ህዝቡ ፖለቲካ እንድወጣ ያደርገኛል። ወደ ድሮው ዘመን ይወስደኛል፤ ካሬቢያን ዳርቻ ላይ አሸዋ ያዘግነኛል።
ከእኔ በተቃራኒ የቆሙ የብሄር ውግንና ፖለቲካ አራማጆች ደግሞ ቴዲን ሰበብ አስባብ እየፈለጉ ይተቹታል። “ንጉስ” የሚሉት የከተሜ አድናቂዎቹ የውግንና ብሄርተኛውን የሚገዳደር አቅም ላይ አልደረሱም።
ቴዲም ሆነ ማናጀሩ እንዲሁም አጠገቡ ያሉ ወዳጆቹ አርቲስቱ በሁለት ብሄርተኛ ወጋኞች መሃል መውደቁን የተረዱ አይመስልም። ቴዲ “ወተት ነጭ ነው!” ቢል የሚነቅፈው አያጣም።
እና:-
አልበሙን ከመልቀቁ በፊት በአድናቂዎቹና በተቺዎቹ መካከል ያለውን ልፊያ እና በስራዎቹ ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ የሚገመግምና የሚያስገመግም አልመሠለኝም።
ከሰሞኑ የሚለቀቀውን #ኢቶሪካ እንደሚያወጣ ከተናገረ ሁለት ሳምንት አለፈው። እነዚህ ተላፊ ወገኖች የቴዲ ሙዚቃ ላይ ሳይሆን ራሱ ቴዲ ላይ ሲላፉ ሁለት ሳምንት ሆናቸው። በመሃል ሙዚቃው የመደመጥ ዕድሉ እንዲሳሳ ይኾናል።
እኔ ቴዲ አጠገብ ያለሁ ሰው ብሆን ኖሮ የምመክረው ኢቶሪካን ምንም ድምጽ ሳያሰማ፤ መግለጫ ሳያስፈልግ፤ ማስታወቂያ ሳይናገር ድንገት እንዲለቀው ነበር። ተጽዕኖ ፈጣሪነቱ የሚፈጥረው ጫጫታ ሙዚቃውን እንዳይረብሽበት “አይረን ዶሙ” ይኼው ነበር።
ቢያንስ አድናቂውም ሆነ ተችው ከሰማው በኋላ ለተለመደው መጓተት ይመጣ ነበር። ያው ነበር ነው።
እንኳን አደረሳችሁ!👍
ከዳንኤል ተፈራ
እንደ አንድ ኢትዮጵያኒስት እና የአፍሪቃ ብሄርተኛ ከብላቴናው በላይ ተስማሚ ዘፋኝ የለኝም
Date:
