102,604 ሰዎች የአዕምሮ ህመምና ተያያዥ ጉዳዮች ህክምና መስጠቱን አምኑኤል አዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ገለፀ

Date:





ሆስፒታሉ ከእነዚህ ታካሚዎች መካከል 98, 803 የሚሆኑት በተመላላሽ የህክምና አገልግሎት የተሰጣቸው መሆኑን ገልጿል።

እንዲሁም፣ ለ1, 421 ለሚሆኑ ህሙማን በአስተኝቶ የአዕምሮ ህክምና፣ በድንገተኛ የአዕምሮ ህክምና ደግሞ ለ2,380 ሰዎች አገልግሎት ተሰጥቷል።

ይህም በ2017 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ለ124,800 ዜጎች በአዕምሮ ህመምና ተያያዥ ጉዳዮች አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ ካቀደው ውስጥ መሆኑን ሆስፓታሉ ገልጿል።

በ9 ወራት ውስጥ 371 የሚሆኑት የህፃናት የአእምሮ፣ 597 ደግሞ የሱስ ህክምናዎች እንዳገኙም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

የፎረንሲክ ህክምናን በተመለከተም፣ “የወንጀልና የፍትሐ ብሔር ተመርማሪዎች በተመላላሽና በተኝቶ 570 ለሚሆኑት አገልግሎቱ ተሰጥቷል” ተብሏል።

በሌላ በኩል፥ በሆስፒታሉ አማካኝ የአስተኝቶ የቆይታ ግዜ በ2016 በጀት ዓመት ከነበረው 36 ቀን በ2017 በጀት ዓመት በ9 ወራት ወደ 33  ቀን፣ አልጋ የመያዝ ምጣኔንም 84% ማድረስ እንደተቻለ ሆስፒታሉ ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA@tikcahethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...