በኢትዮጵያ የሚገኙ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች አገልግሎት እየሰጡ ያሉት ለሀገሪቱ ህዝብ 3 በመቶ ለሚሆነው ብቻ መሆኑ ተገለጸ። ይህ ደግሞ በቂና ፍትሃዊ የሆነ የመድን ሽፋን እየተሰጠ አለመሆኑን ያሳያል።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ 18 የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ሲኖሩ፣ ከእነዚህ ውስጥ 13ቱ ብቻ የህይወት መድን አገልግሎት ይሰጣሉ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በ2013 ዓ.ም. ባካሄደው ጥናት፣ ከኢንሹራንስ ኩባንያዎቹ 55 በመቶ የሚሆኑት ቅርንጫፎቻቸው በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እንደሚገኙ አመላክቷል።
የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽመልስ ገድለጊዮርጊስ እንደተናገሩት፣ ይህ የተደራሽነት ውስንነት ፍትሃዊ የመድን ሽፋን እንዳይኖር አድርጓል።
ብስራት እንደዘገበዉ አንድ በዓለም ባንክ እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ትብብር የተሰራ ጥናት እንደሚያሳየው፣ ኢትዮጵያውያን የህይወት መድን የማይገዙበት ትልቁ ምክንያት የግንዛቤ እጥረት ነው። የኢንሹራንስ ኩባንያዎችና ቅርንጫፎቻቸው በአቅራቢያ አለመገኘትም ሌላኛው ምክንያት መሆኑ ተጠቁሟል።
የቅዳሜ ገበያ
