“ለንደን ኤፍ ኤም ” የተሰኘ ራድዮ ጣቢያ ሥራ ሊጀምር ነው

Date:

በዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ ያተኮረ እና መረጃን በሦስት ቋንቋዎች የሚያቀርብ “ለንደን ኤፍ ኤም 102.1” የተሰኘ የሬድዮ ጣቢያ ተቋቁሞ የሙከራ ስርጭቱን መጀመሩን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ይፋዊ መግለጫ ተሰጧል።

“ለንደን ኤፍ ኤም 102.1” በኢትዮጵያ ካለው “ናፍቆት ሚዲያና ማስታወቂያ ስራዎች” ድርጅት ጋር በአጋርነት እንደሚሰራ በመግለጫው መርሃግብር ላይ አስታውቋል።

የናፍቆት ሚዲያና ማስታወቂያ ስራዎች ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ጋዜጠኛ ናፍቆት ዩሱፍ እንደገለጹት፣ በስደት የሚኖሩ ወገኖች የመረጃ ክፍተት በመኖሩ ለከፍተኛ እንግልት እና ስቃይ የሚጋለጡበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ለመቅረፍ በማሰብ ለንደን ኤፍ ኤም 102.1 መፍትሔ ይዞ መቅረቡን ገልጸዋል።

በዩናይትድ ኪንግደም ያሉ ስደተኞች በመረጃ እጦት እና አማካሪ በማጣት የሚደርስባቸውን ችግር ለማቅለል እና መረጃው በቀላሉ እንዲደርሳቸው በአማርኛ፣ በኦሮምኛና በትግርኛ ቋንቋዎች አገልግሎት እንደሚሰጥ በመግለጫው ላይ ተገልጿል።

ለሃገር ውስጥ ነጋዴዎች፣ አምራቾች እና አገልግሎት ሰጪዎች ምርትና አገልግሎታቸውን በዩኬ ለሚገኙ ዲያስፖራዎች እንዲያስተዋውቁ መድረክ በመሆን፣ ለዜጎች የገበያ ዕድል መፍጠርና ለሃገር የውጭ ምንዛሬ ማምጣት አንዱ ዓላማው እንደሆነ በመግለጫው ተገልጿል።

የለንደን ኤፍ ኤም 102.1 መስራች እና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ሽፈቀ አደም ከዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) እንደተናገሩት፣ ጣቢያው በዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) የስደተኛ ጉዳዮች ዕገዛና የማማከር አገልግሎት ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ገልጸው በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ አድማጮች ከሃገር ከመውጣታቸው በፊት ስለ ስደተኛ ጉዳዮች ያሉትን ደንቦችና እውነታዎች በተመለከተ ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኙ ያስችላል ብለዋል።

በሌላ በኩል ወ/ሮ ኮክ አስፋ ጣቢያውን ካቋቋሙት መካከል አንዱ ሲሆኑ በሞያቸው ጋዜጠኛ፣ ኤቨንት ኦርጋናይዘርና የግራፊክስ ባለሙያ በመሆን የጣቢያው ተባባሪ መስራች ናቸው።

እነዚህ ሁለቱ ኢትዮጵያውያን በእንግሊዝ እና በሌሎች ሃገራት ከሚገኙ የመገናኛ ባለሙያዎች፣ ጋዜጠኞች፣ የአስተዳደርና ተጓዳኝ ዘርፎች ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት ተቋሙን እንደመሠረቱት ተገልጿል።

“ለንደን ኤፍ ኤም 102.1” ሬድዮ በበየነመረብ አማካኝነት ስርጭት የጀመረ በቅርቡ በመደበኛ የሬዲዮ ስርጭት እንደሚጀምር ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...