ምንገድ ላይ

Date:

(በእውቀቱ ስዩም)


በቀደም ከሆነ ቦታ ተነስቼ ወደ አልሆነ ቦታ ስራመድ ኡራኤል ፊትለፊት ካለው አስፋልት ላይ ስደርስ የሚገርም ነገር ተከሰተ፤ አንድ የጎዳና ተዳዳሪ ቡሌ በፌስታል, ሸክፎ አስፋልት እያቁዋረጠ ሳለ አንድ ሞተረኛ ከላይ ሲንደርደር መጥቶ ደንብቆ ጣለው ፤ የሸገር ሞተረኞች ለምን እንደሚካልቡ አይገባኝም፤

አለምን ከጥፋት የሚታደግ መልክት ለማድረስ የሚነዱ እንጂ የጠወለገ በለጨ የጫኑ አይመስሉም፤
ሞተረኛው ከሞተሩ ተስፈንጥሮ አስፋልቱ ዳር ተዘረረ ፤ ሞተሩ ግን በራሱ ፈቃድ እየበረረ ሂዶ ባቅራቢያው ከሚገኝ ጋራጅ ውስጥ ገብቶ ተሰወረ፤ የጎዳናው ሰውየ ተሽቀንጥሮ መንገዱ ጠርዝ ላይ ተገኘ፤ ወድያው ባካባቢው የነበረው ህዝብ ሞተረኛውን እና የጎዳናውን ሰውየ ተካፍለው ከበብ ከበብ አድርገው ቆሙ፤ ብብዙዎች ፊት ላይ ሀዘን በግልፅ ይነበባል ፤ ቢያንስ ከሁለት አንዱ አለመሞታቸው ብዙዎችን ያስደበረ ይመስለኛል ፤


እኔ ሁሌም ከተጎጂው ጎን መሰለፍ ስለሚያስደስተኝ ፣ ከጎዳና ተዳዳሪው አጠገብ ቆምኩ፤ ተጎጂው ቀና ብሎ አየኝ፤ መላከ ሞትን ያባረረ ኡራኤል መስየ ታይቸው ይሆንን ብየ ራሴን ሸነገልሁ፤


የጎዳናው ሰውየ የፈራሁትን ያህል አልተጎዳም፤ ደጋግሞ የመገጨት ልምድ ያካበተ ይመስላል፤ የቀኝ እግሩ መሀል አገዳ ላይ ብቻ የመድማትና የመጫጫር ምልክት አየሁ፤


-አይዞህ ወንድም ጥላ! በዚች እግርህን ታይበት ‘ አልሁና ከቦርሳየ ውስጥ ሁለት መቶ ብር በማውጣት ዘረጋሁለት፤


በልግስናየ ልቡ ተነክቶ ተጠምጥሞብኝ ያለቅሳል የሚል ግምት ነበረኝ፤
‘እናትህ ትጎዳ ! (በትክክል ያለኝ እንኩዋ ከ-ትጎዳ-ይከፋል )፤ በሁለት መቶ ብር ምንላቀቅ መስሎሀል?’ አለና እጅጌየን ጥቅጥቅ አርጎ ያዘኝ;
ክፉኛ አንደዞረበት ተገለጠልኝ፤


‘አይዞህ ዠለሳዊ ! በዚህ ደግሞ ጭንቅላትህን ታይበት’ አልሁና ቸክ ፈርሜለት ጉዞየን ቀጠልሁ፤ የስቃይ ትርጉምና የሰው ልጅ የመጨረሻው ነፃነት ስቃይና መከራ የሕይወት የማይቀሩ ክፍሎች ናቸው፤ ልክ እንደ መወለድና እንደ መሞት፡፡

ሕይወት ትርጉም አላት ከተባለ፣ እስከ መጨረሻው እስትንፋስ ድረስ ባለው ስቃይም ውስጥ ትርጉም ሊኖር ይገባል። እዚህ ላይ ግን ትልቅ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል፤ እኔ እያወራሁ ያለሁት ስለማይቀረውና ልንቆጣጠረው ስለማንችለው ስቃይ እንጂ፣ በፈቃደኝነት ስለሚፈለግ ወይም መፍትሔ ስላለው መከራ አይደለም።

መከላከል የሚቻልን ስቃይ በዝምታ መቀበል ጀግንነት ሳይኾን ራስን መበደል ነው። ነገር ግን ሁኔታዎችን ሙሉ በሙሉ መለወጥ በማንችልበት ጥግ ላይ ስንደርስ—ለምሳሌ የማይድን በሽታ ሲገጥመን ወይም በግፍ እስር ውስጥ ስንወድቅ—ትልቁ ፈተና የሚጀምረው እዚያ ላይ ነው።


ሁኔታዎችን መለወጥ ካልቻልን፣ ራሳችንን እንድንለውጥ እንገደዳለን፡፡ ይህ ደግሞ የሰው ልጅ ማንም ሊቀማው የማይችለው የመጨረሻው ነፃነት ነው። አንድን ሰው ንብረቱን፣ ማዕረጉን፣ አልፎ ተርፎም አካላዊ ነፃነቱን ልትወስዱበት ትችላላችሁ፤ ነገር ግን በሚገጥመው ማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የትኛውን የአስተሳሰብ አቅጣጫ መምረጥ እንዳለበት (To choose one’s attitude) የመወሰን መብቱን ልትቀሙት አትችሉም።

በካምፕ ውስጥ በነበርንበት ጊዜ፣ የራሳቸውን የመጨረሻ እንጀራ ቆርሰው ለሌሎች የሚያካፍሉ፣ ሰዎችን የሚያጽናኑ ጥቂት ምርጥ ሰዎችን አይቻለሁ። እነሱ በአካል እስረኞች ቢኾኑም በነፍስ ግን ከሁሉም በላይ ነፃ ነበሩ። ያሳለፉት ስቃይ ዝም ብሎ የባከነ አልነበረም፤ ይልቁንም ውስጣዊ ማንነታቸውን ያጠነከሩበት፣ የሰው ልጅን ክብር ያስመሰከሩበት መሠረት እንጂ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...