በእስራኤል ባለፉት 24 ሰዓታት 191 ሰዎች ቆሰሉ

Date:

የእስራኤል የጤና ሚኒስቴር ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በነበረው ውጥረት 191 እስራኤላውያን ቆስለው ወደ ሆስፒታሎች መግባታቸውን ይፋ አድርጓል።

ከተጎዱት መካከል ወታደሮችና ሲቪሎች የሚገኙበት ሲሆን፣ የአንዳንዶቹ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑ ተገልጿል። ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ አንስቶ እስካሁን 2,339 ሰዎች የሕክምና ዕርዳታ ማግኘታቸውን ዘ ታይምስ ኦፍ እስራኤል ዘግቧል።

በሌላ በኩል፣ ግጭቱ እየተባባሰ መምጣቱን ተከትሎ በቤሩት የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በሊባኖስ ለሚገኙ ዜጎቹ አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል።

ዜጎቹ የምግብ፣ የውሃና የመድኃኒት አቅርቦት በማዘጋጀት አስተማማኝ መጠለያ ውስጥ እንዲቆዩ አሳስቧል።

በሊባኖስ በኩል ደግሞ በእስራኤልና በሂዝቦላ መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውንና የሟቾች ቁጥር ቢያንስ 486 መድረሱን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...